በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ረሃብ አድማ ላይ የነበረው የፍልስጤም እስረኛ ሕይወቱ አለፈ


የ45 ዓመቱ ካድር
የ45 ዓመቱ ካድር

በእስራኤል እስር ላይ የነበረ አንድ የፍልስጤም እስላማዊ ጂሃድ ቡድን አባል ለሶስት ወራት የረሃብ አድማ ካደረገ በኋላ ዛሬ ሕይወቱ ማለፉ ተዘግቧል።

የ45 ዓመቱ ካድር አድናን በታሰረበት ክፍል ውስጥ ራሱን ስቶ ከተገኘ በኋላ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ የነበረ ቢሆንም ህይወቱ ማለፉ ታውቋል።

ኢስላሚክ ጂሃድ የተሰኘው ቡድን አባል የሆነው አድናን ባለፈው ጥር መጨረሻ በሽብርተኝነት ተሳትፏል በሚል በዌስት ባንክ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ፣ የረሃብ አድማውን ጀምሮ የነበረ ሲሆን፣ ከዚህ በፊትም በተመሳሳይ በቁጥጥር ሥር በዋለበት ወቅቶችም የረሃብ አድማ በማድረጉ ይታወቃል።

የአድናን ሞት እንደተሰማ በሃማስ ቁጥጥር ስር ባለው ከጋዛ ሰርጥ ሶስት ሮኬቶች መተኮሳቸውን የእስራኤል ሠራዊት አስታውቋል። ሮኬቶቹ ሰውን ሳጎይዱ ባዶ መሬቶች ላይ ማረፋቸውንም አስታውቋል።

ኢስላሚክ ጂሃድ የተሰኘው ቡድን የአድናንን ሞት አውግዞ፣ በእስራኤል ላይ የሚደረገው ትግል እንደሚቀጥል አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG