በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ጋዛን ይዞ የመቆየት ፍላጎት እንደሌላት ኔታንያሁ አስታወቁ


ፎቶ ፋይል፦ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ
ፎቶ ፋይል፦ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ

እስራኤል ጋዛን ይዞ ለመቆየት ፍላጎት እንደሌላት፣ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ ትላንት ኀሙስ፣ ከፎክስ ኒውስ ጋራ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ተናግረዋል።

በዚኽ ሳምንት መጀመሪያ ላይ፣ “እስራኤል የጋዛን የጸጥታ ሥራ እና ኹኔታ ትቆጣጠራለች፤” ሲሉ፣ ኔታንያሁ ቢናገሩም፣ ዝርዝር ነገሮችን ግን አልገለጹም ነበር።

የሐማስ ታጣቂ በእስራኤል ላይ ጥቃት እንዳይሰነዝር፣ እምነት የሚጣልበት ኃይል በጋዛ ውስጥ መኖር እንዳለበት፣ ኔታንያሁ አመልክተዋል።

“ግብ አስቀምጫለኹ። የጊዜ ሰሌዳ ግን አላወጣኹም፤ ምክንያቱም ጊዜ የሚፈጅ ጉዳይ ነው፤” ያሉት ኔታንያሁ፣ የሰላማውያን ሰዎችን ጉዳት ለመቀነስና አሸባሪ ብለው በጠሩት ሐማስ ላይ ጥቃቱን ለማጠናከር እየሠሩ እንደኾነ ተናግረዋል። “እስከ አሁን በጥሩ አኳኋን እየሔደ ነው፤” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ዋይት ሐውስ፣ በቀናት የሚቆጠር ሰብአዊ ተኩስ አቁም እንዲኖር ላቀረበው ጥያቄ የመለሱት ኔታንያሁ፣ በሐማስ ላይ የሚደረገው ጥቃት እንደማይቋረጥ አጽንተው፣ እያለፈ ግን ሲቪሎች ከውጊያ ቀጣናው እንዲወጡ ለማስቻል፣ ለሰዓታት የሚቆጠር እፎይታ እንደሚኖር አስታውቀዋል።

በጦርነቱ እስከ አሁን፣ 10ሺሕ800 እንደተገደሉና ከእኒኽም ከሦስት እጁ ሁለቱ ሴቶች እና ሕፃናት እንደኾኑ፣ በሐማስ የሚተዳደረው የጤና ሚኒስቴር ገልጿል። ቁጥሩን በገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ ባይቻልም፣ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከዚኽ ቀደም ያወጣቸው የነበሩ አኀዞች፣ ተኣማኒ እንደነበሩ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውሷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG