በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋዛ የኢንዶኔዢያ ሆስፒታል ዙሪያ ውጊያ እንደተካሔደ ተነገረ


በጋዛ የኢንዶኔዢያ ሆስፒታል ዙሪያ ውጊያ እንደተካሔደ ተነገረ
በጋዛ የኢንዶኔዢያ ሆስፒታል ዙሪያ ውጊያ እንደተካሔደ ተነገረ

በሰሜን ጋዛ በሚገኘው የኢንዶኔዢያ ሆስፒታል አካባቢ ውጊያ ተካሒዶ እንደነበር፣ የአሶሽየትድ ፕሬስ ዜና ወኪል፣ በሐማስ የሚተዳደረውን የጤና ሚኒስቴር እና አንድ ሠራተኛን ጠቅሶ ዘግቧል።

ከባድ መሣሪያ የሆስፒታሉን ሁለተኛ ፎቅ ሲመታ፣ 12 ሰዎች እንደተገደሉ ዘገባው አመልክቷል። የእስራኤል መከላከያ ኀይል በጉዳዩ ላይ ያለው የለም።

የኢንዶኔዢያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬንቶ ማርሱዲ፣ ጥቃቱን አውግዘው እስራኤልን ተጠያቂ አድርገዋል። ጥቃቱ፣ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ሕግን እንደጣሰም፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አክለው ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ እስራኤል፥ “በሺፋ ሆስፒታል ሥር የተቆፈረ የምድር ውስጥ መተላለፊያ ነው፤” ያለችውን ምስል ይፋ አድርጋለች፡፡ ሐማስ በበኩሉ ውንጀላውን አስተባብሏል።

በጋዝ ሰርጥ ውስጥ እየተካሔደ ባለው ውጊያ፣ አምስት ተጨማሪ ወታደሮቿ እንደተገደሉባት እስራኤል አስታውቃለች፡፡ ይህም፣ ግጭቱ ከተጀመረ አንሥቶ የሞቱትን የእስራኤል ወታደሮች ቁጥር 64 አድርሶታል።

በሌላ በኩል፣ ትላንት እሑድ፣ ከሺፋ ሆስፒታል የወጡትና ከጊዜያቸው ቀድመው የተወለዱ 28 ሕፃናት፣ ዛሬ ግብጽ ደርሰዋል። ሕፃናቱን ከሆስፒታሉ የማስወጣቱ ሥራ እጅግ ከባድ እና አደገኛ እንደነበር ተነግሯል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG