በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል ወታደራዊ ኃይል ጋዛ ላይ የአየር ድብደባ አደረገ


የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሜን ኔታንያሁ ሃገራቸው ጋዛ ካሉት ፍሊስጤማውያን ተቃዋሚዎች ጋር እየተካሄደ ያላውን ግጭት ማባባስ ባልትፈልግም ለሚደርስባት እያንዳንዱ ጥቃት ምላሽ ትሰጣለች ብለዋል።

ኔታንያሁ የካቢኔ ስብሰባ ሲጀመር ባደረጉት ንግግር እስላማዊው ጂሃድ ያለው አማራጭ “ጥቃቶቹን ማቆም ወይም ተጨማሪ ምቶችን መቀበል ነው” ሲሉ ዝተዋል።

የእስራኤል ወታደራዊ ኃይል ዛሬ ጋዛ ላይ የአየር ድብደባ አካሄዷል። ጋዛ ያሉት ታቃዋሚዎች በበኩላቸው እስራኤል ላይ የሮኬቶች ተኩስ ከፍተዋል።

የፍሊስጤም የጤና ጥበቃ ባለሥጣኖች በገለጹት መሰረት ውጊያው ትላንት ማክሰኞ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ 18 ፍሊስጤማውያን ተገድለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG