እስራኤል ዛሬ ሰኞም የጋዛ ሠረጥን እና በሌባኖስ የሚገኙ የሄዝቦላ ኢላማዎችን ደብድባለች፡፡
ከበባ ውስጥ ያለችው ጋዛ ሰማይ ዛሬም በጭስ ጠቁሮ ታይቷል።
ፍልስጤማውያኑ በጥቃት ወቅት እንዲደበቁ የተነግራቸው ሥፍራዎች ጭምር በጦር አውሮፕላኖች ተደብድበዋል ተብሏል። በግብጽ መተላለፊያ ራፋ በኩል ርዳታ ወደ ጋዛ ለሁለተኛ ግዜ ቢገባም፣ በቂ እንዳልሆነ ተነግሯል።
እስራኤል አሁንም ለሁለት ሳምንታት ኤሌክትሪክ ወደተቋረጠባት የጋዛ ሰርጥ ነዳጅ እንዲገባ እንዳልፈቀደች ታውቋል።
ሆስፒታሎች የሕክምና ቁሳቁስ እና ለጄኔሬትሮች የሚሆን ነዳጅ እጥረት እንዳለባቸው አስታውቀዋል።
የፍልስጤማውያን የጤና ሚኒስቴር ትናንት እሁድ እንዳስታወቀው፣ በጋዛ ሠርጥ የሟቾች ቁጥር 4ሺሕ 651 ሲደርስ፣ 14ሺሕ 254 ስዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ሐማስ የመዋጋት አቅሙ እስኪያከትም ድረስ ጥቃቱን እንደማያቆሙ የእስራኤል ባለሥልጣናት በመናገር ላይ ናቸው።
በሌላ በኩል፣ የአውሮፓ ኅብረት የውጪ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት ጆሴፕ ቦረል፣ ለስብዓዊ ሥራ ሲባል ግጭቱ ቆም ማለት እንዳለበት ለዜና ሰዎች ተናግረዋል።
መድረክ / ፎረም