በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ከጋዛ ሁለተኛ-ትልቁ ከተማ ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ አዘዘች


ፍልስጤማውያን በሃን ዩኒስ ሆስፒታል በቦምብ ጥቃት ለተገደሉ ዘመዶቻቸው አዝነዋል፣ እአአ ኅዳር 3/2023
ፍልስጤማውያን በሃን ዩኒስ ሆስፒታል በቦምብ ጥቃት ለተገደሉ ዘመዶቻቸው አዝነዋል፣ እአአ ኅዳር 3/2023

የእስራኤል ወታደሮች በሐማስ ታጣቂዎች ላይ ያነጣጠረ የምድር እና የአየር ላይ ድብደባ አጠናቅረው በቀጠሉበት ወቅት፣ በጋዛ ሰርጥ ሁለተኛው ትልቁ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ እስራኤል ሰኞ እለት አሳስባለች።

የእስራኤል ጦር በሰሜናዊ ምስራቅ በሚገኘው ሃን ዩኒስ ከተማ ውስጥ ባሉ ሰፈሮች የሚኖሩ ሰዎችን ለደህንነታቸው ሲሉ እንዲለቁ እና በስተደቡብ ራቅ ብለው ወደሚገኙ አካባቢዎች እንዲሄዱ ነው የነገሯቸው።

ሃን ዩኒስ በደቡብ ጋዛ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ እስራኤል በሰሜናዊው የጋዛ ሰርጥ ክፍል ዘመቻዋን ስትጀም በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ሸሽተው የተጠለሉበት ከተማ ነው።

እስራኤል ጥቃት ካደረሰችባቸው አካባቢዎች ሰዎች እንዲሸሹ ተደጋጋሚ ማስታወቂያዎችን ብታወጣም፣ በጋዛ በቂ የኤሌክትሪክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት በሌለበት ሰዎች መረጃ ማግኘት የማይችሉ በመሆናቸው ከተባበሩት መንግስታት ባለስልጣንት ከፍተኛ ትችት ይደርስባታል።

ሰማኒያ ከመቶ የሚሆነው የጋዛ ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው በተፈናቀሉበት እና ብዙዎቹ በተጨናነቁ መጠለያዎች ውስጥ በሚገኙበት ወቅት ያለው የሰብዓዊ ሁኔታም አሳሳቢ መሆኑን ገልጾ የመንግስታቱ ድርጅት አስጠንቅቋል።

የእስራኤል ወታደሮች ቀደም ሲል ሲቪሎች ወደተሰደዱባቸው እና ወደተጠለሉባቸው አካባቢዎች ዘመቻውን ማስፋታቸው እና በደቡባዊ ጋዛ ግጭት መባባሱ፣ በግብፅ በኩል በሚገባው ሰብዓዊ እርዳታ ስርጭት ላይ ተፅእኖ እንደሚያሳድርም ተመልክቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤል ጦር ሰኞ እለት ባወጣው መግለጫ፣ በሰሜናዊ ጋዛ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ የሐማስ ወታደራዊ ጣቢያዎችን ጨምሮ፣ በአንድ ምሽት 200 የሐማስ ኢላማዎች ላይ ጥቃት ማድረሱን አስታውቋል።

ለአንድ ሳምንት የዘለቀው የተኩስ ማቆም ስምምነት አርብ እለት ካበቃ በኃላ ቢያንስ 300 ፍልስጤማውያን የተገደሉ ሲሆን፣ በዚህም ጦርነቱ በጥቅምት ወር ከጀመረ አንስቶ ጋዛ ውስጥ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 15ሺህ ሁለት መቶ መድረሱን እና 40 ሺህ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የፍልስጤም ጤና ሚኒስትር አስታውቋል። ከተጎጂዎቹ 70 ከመቶ የሚሆኑት ሴቶች እና ህፃናት መሆናቸውም ተገልጿል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG