በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ማክሮን እየሩሳሌምን እየጎበኙ ባሉበት ጋዛን መደብደቧን ቀጥላለች


የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፣ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እአአ ጥቅምት 24/2023.
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፣ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እአአ ጥቅምት 24/2023.

እስራኤል ሃማስ በሚቆጣጠረው ጋዛ ውስጥ ባሉ ኢላማዎች ላይ ለሊቱን እስከ አዲስ ዙርብ የአየር ድብደባ አካሄደች። በድብደባው ከባህር ዳር አቅራቢያ ከሚገኝ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ የነበሩ ሰዎችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል’ ሲሉ የፍልስጤም ባለስልጣናት ተናግረዋል።

በሌላ በኩል፡ ሃማስን ጨርሶ ለማጥፋት ከበባ ውስጥ በምትገኘው የፍልስጤም ግዛት የእግረኛ ጦሩን ለማዝመት የያዘውን ዕቅድ ለጊዜው የገታው የእስራኤል ጦር ሰራዊት፡ ባለፉት ሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ ከ400 በላይ ቦታዎችን መውደሙን አስታውቋል። ከአንድ ቀን በፊትም 320 ጊዜ የአየር ድብደባ መፈጸሙ ተዘግቧል።

በሃማስ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር የምትገኘው ጋዛ የጤና ሚኒስቴር በበኩሉ፡ የሟቾች ቁጥር በገለልተኛ ደረጃ ሊረጋገጥ ባይቻልም 704 ሰዎች መገደላቸውን አመልክቷል። የፍልስጤም የጤና ሚኒስቴሩ በዛሬው መግለጫው ከሁለት ሳምንታት በፊት በተጀመረው ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 5,791 ደርሷል’ ሲል አክሏል።

ይህ ያሁኑ ዙር የእስራኤል የዓየር ድብደባ ዜና የተሰማው፤ ‘ለእስራኤል ያላቸውን አጋርነት ለመግለጥ እና በጋዛ ያሉ ሲቪሎች ደህንነት

እንዲጠበቅ’ የሚሉ ጣምራ መልዕክቶችን ይዘው ወደ እየሩሳሌም የመጡት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እስራኤልን እየጎበኙ ባሉበት ወቅት ነው። ማክሮን የመስከረም ሃያ ስድስቱን ጥቃት ተከትሎ እስራኤልን የጎበኙ ሁለተኛው መሪ መሆናቸው ነው።

“ሃማስ በአይሁዳዊቱ አገር ላይ የሰነዘረው እና ከ1,400 በላይ ሰዎችን የገደለው ጥቃት መቼም ቢሆን የማይረሳ ነው” ሲሉ ለእስራኤሉ ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ የተናገሩት ማክሮን፤ በሐማስ የተያዙትን ከ200 በላይ ታጋቾችን ማስፈታት ከሁሉም ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል’ ብለዋል።

ማክሮን አክለውም “በዚህ ከሽብርተኝነት ጋር በሚደረግ ጦርነት ብቻችሁን ያለመሆናችሁን በእርግጠኝነት እንድትረዱ እፈልጋለሁ።” ማለታቸው ተዘግቧል።

ዘግይቶም ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ማክሮን “በኢራቅ እና በሶሪያ እስላማዊውን ጽንፈኛ ቡድን አይሲስ’ን ለመርታት የሚታገለውዓለም አቀፍ ጥምረት ሃማስንም መዋጋት አለበት” ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG