በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ጋዛንና ሊባኖስን በአየር ደበደበች


የሊባኖስ ወታደር በደቡባዊ ሊባኖስ፤ በኩላይላ
የሊባኖስ ወታደር በደቡባዊ ሊባኖስ፤ በኩላይላ

እስራኤል፣ በጋዛ እና በሊባኖስ ላይ፣ ዛሬ ጠዋት የአየር ድብደባ ፈጽማለች። የአየር ድብደባው፣ እስላማዊ ቡድን ለኾነው ለሐማስ "የሮኬት ጥቃት የተሰጠ ምላሽ" እንደኾነ የገለጸችው እስራኤል፣ ትላንት ኀሙስ፣ ከሊባኖስ አቅጣጫ በተተኮሱ በደርዘን በሚቆጠሩ ሮኬቶች፣ ጥቃት እንደተፈጸመባት አስታውቃለች።

ዛሬ ማለዳ፣ የእስራኤል ጀቶች፣ አንዳንድ የጋዛን አካባቢዎች ሲደበድቡ አርፍደዋል። ድብደባው ያነጣጠረው፣ በመሣሪያ ማምረቻዎች እና የመሬት ውስጥ ለውስጥ መደበቂያ ጉድጓዶች ላይ እንደኾነ የእስራኤል ጦር አስታውቋል።

ጦሩ አክሎ እንዳለው፣ በደቡብ ሊባኖስ የሐማስ ይዞታ የኾነን ሥፍራም ደብድቧል። ታየር በተሰኘችው የደቡብ ሊባኖስ የወደብ ከተማ፣ ፍንዳታ እንደነበር፣ አንድ የሊባኖስ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

በሊባኖስ እና በጋዛ ድንበሮች ላይ፣ ወታደራዊ ኃይሏን ማጠናከሯን ያስታወቀችው እስራኤል፣ “ለሚከሠቱ ማንኛውም ነገሮች ዝግጁ ለመኾን ነው፤” ስትል አስገንዝባለች።

በእስልምና እምነት፣ ሦስተኛው ቅዱስ ቦታ ተደርጎ በሚታመነው አል-አቅሳ መስጊድ፣ በእስራኤል ፖሊስ እና በፍልስጥኤማውያን መሀከል፣ በቅርቡ ግጭት ከተከሠተ ወዲህ፣ በአካባቢው ውጥረት ጨምሯል።

በዛሬው የዓርብ ጸሎት ሥነ ሥርዓትም፣ ሐማስን የሚያወድሱ መፈክሮች የሚያሰሙ ፍልስጥኤማውያን ከፖሊስ ጋር ጋጭተዋል፤ ሲል አሶስየትድ ፕረስ ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG