በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የአየር ጥቃት አደረሰች


እስራኤል ዛሬ አርብ ጋዛ ሰርጥ ላይ የአየር ጥቃት አድርሳለች፡፡
እስራኤል ዛሬ አርብ ጋዛ ሰርጥ ላይ የአየር ጥቃት አድርሳለች፡፡

እስራኤል ዛሬ አርብ ጋዛ ሰርጥ ላይ የአየር ጥቃት አድርሳለች፡፡ ጥቃቱን ያካሄደችው ታጣቂዎች ከፍልስጥዔም ግዛቶች ሮኬት መተኮሳቸውን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የእስራኤል ኃይሎች በዌስት ባንክ ባካሄዱት ወረራ ሰዎች ከተገደሉ ወዲህ በሁለቱ ወገኖች መካከል ውጥረቱ እየተባባሰ ሄዷል፡፡

የእስራኤል የጦር ኃይል በእስራኤላውያን ላይ በተደጋጋሚ ተኩሰዋል ያላቸውን የእስላማዊ ጂሃድ ታጣቂዎች ዒላማ በማድረግ ቢያንስ ሁለት ጊዜ የአየር ጥቃት ማድረሱን አመልክቷል፡፡

ሁለቱም ወገኖች በሰው ላይ ስለደረሰ ጉዳት የተናገሩት ነገር የለም፡፡ ከጋዛ ሰርጥ የተተኮሱት ሮኬቶች የእስራኤል የአየር ጥቃት መከላከያ ኃይሎች መትተው እንደጣሏቸው ገልጸዋል፡፡

የዛሬ የተኩስ ልውውጥ የተካሄደው ትናንት የእስራኤል ወታደሮች ጂኒን ውስጥ በሚገኝ የስደተኛ ካምፕ ወርረው ዘጠኝ ሰዎችን መግደላቸውን ተከትሎ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ከጋዛ ስለተተኮሱ ሮኬቶች አስካሁን ኅላፊነት የወሰደ ወገን ባይኖርም ሃማስ እና እስላማዊ ጂሃድ የተባለው ቡድን እስራኤል ጂኒን ላይ ላደረሰችው ጥቃት አጸፋ እንመልሳለን ብለው ዝተው ነበር፡፡

XS
SM
MD
LG