ዋሺንግተን ዲሲ —
የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች ዛሬ በጋዛ ሰርጥ እስላማዊ ጂሃድ የተባለው አማፂ ቡድን ይዞታዎችን ዒላማ ያደረገ ጥቃት አካሂደዋል።
ጥቃቱ የተካሄደው ታጣቂዎች ከጋዛ ደቡባዊ እስራኤል ውስጥ ወዳሉ በርካታ አካባቢዎች ቢያንስ ሃያ አምስት መድፎች መተኮሳቸውን የእስራኤል የመከላከያ ኃይሎች ባስታወቁ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ መሆኑ ታውቋል።
ከጋዛ ከተተኮሱት መድፎች አብዛኞቹን የሚሳይል መከላከያዎችን ደርሶ እንዳከሸፈ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ባዶ ሜዳ ላይ ማረፋቸውን ነው - የእስራኤል መከላከያ ያስታወቀው፡፡ በሰው ላይ ስለደረሰ ጉዳት አልተዘገበም፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ