በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ከ50 በላይ ፍልስጤማውያን በተገደሉበት ጥቃት ሁለት ታጋቾችን አስለቀቀች


በደቡባብዊ ጋዛ ራፋህ ከተማ የእስራኤል ወታደራዊ ዘመቻ ጋር ተያይዞ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እየሸሹ እአአ የካቲት 12/2023
በደቡባብዊ ጋዛ ራፋህ ከተማ የእስራኤል ወታደራዊ ዘመቻ ጋር ተያይዞ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እየሸሹ እአአ የካቲት 12/2023

የታገቱትን ለማስለቀቅ ከሚደረገው የእስራኤል ወታደራዊ ዘመቻ ጋር ተያይዞ በተፈጸመው የአየር ጥቃት ቢያንስ 50 ሰዎች መገደላቸውን ደቡባብዊ ጋዛ ራፋህ ከተማው ውስጥ የሚገኙ የሆስፒታል ባለሥልጣናት ተናገሩ፡፡

የአቡ የሱፍ አል ናጃር ሆስፒታል ዳይሬክተር ዶ/ር አቡ ማርዋን አል-ሐምስ ዛሬ ሰኞ እንደተናገሩት ከሟቾቹ መካከል ሴቶች እና ህጻናት ይገኙበታል።

በራፋህ አቡ ዩሱፍ አል-ናጃር የማቾች ቤተሰቦች በአስክሬኖቹ ላይ ተደፍተው በሚያለቅሱበት ሆስፒታል ውስጥ የራሱ ጋዜጠኛ ቢያንስ 50 አስከሬኖችን መቁጠሩን አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

የእስራኤል ኃይሎች ዛሬ ሰኞ ማለዳ ላይ ጋዛ ውስጥ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለት አንድ የአፓርትመት ህንጻ በመውረር በተኩስ ልውውጥ መካከል ሁለት ታጋቾችን ማስለቀቅ መቻላቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡

ምንም እንኳ የተለቀቁት የታጋቾቹ ቁጥር አነስተኛ ቢሆንም ለእስራኤል ስኬት ትልቅ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡

መሃመድ ዞሮብ የተባሉት የአካባቢው ነዋሪ ለአሶሴይትድ ፕሬስ ሲናገሩ “ በአካባቢው ግጭት ነበር በሁሉም አቅጣጫ ይካሄድ ከነበረው የአየር ጥቃት ለማምለጥ ልጆቻችንን ይዘን እንሯሯጥ ነበር “ ብለዋል፡፡

“ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ብንሄድ ከ17-18 በላይ የሚደርሱ የአየር ጥቃቶች ተካሂደዋል” ሲሉም ነዋሪው አክለዋል፡፡

የእስራኤል እግረኛ ኃይሎችን የደገፈው የአየር ጥቃት የተጨናነቀውን የራፋ አካባባቢ ያጠቃው ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ ሲሆን፣ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ግድም ላይ በአካባቢው በርካታ ፍንዳታዎች የተሰሙ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

በጋዛ የሚገኘው የሐማስ ጤና ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አሽራፍ አልቂድራ በአየር ጥቃቱ ቢያንስ 67 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል፡፡

የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ሪድ አድሚራል ዳንኤል ሃጋሪ በአየር ኃይሉ የተደገፈው ልዩ ኃይሉ በተኩስ መካከል ሁለተኛው ፎቅ ወደ ሚገኘው አፓርትመንት በማምራት በሐማስ ቁጥጥር ሥር የነበሩ ሁለቱን ታጋቾች ማስለቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡

የ60 እና የ70 ዓመት እድሜ እንዳላቸው የተነገረላቸው ታጎቾች ባላፈው ጥቅምት ወር በሐማስ ከታገቱት 250 ሰዎች መካከል መሆናቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG