ሶሪያ፣ በደማስቆ እና አሌፖ የሚገኙ የአየር ማረፊያዎቿን፣ እስራኤል በሚሳኤል እንዳጠቃችባት ገልጻ፣ ዛሬ ክስ አሰምታለች።
ክሱ የተሰማው፣ በእስራኤል እና በሐማስ ታጣቂ መካከል የተፋፋመው ግጭት፣ የመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣናን ወደሚያጥለቀልቅ ጦርነት እንዳያመራ ስጋቱ ባየለበት ወቅት ነው።
በሌላ በኩል፣ የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ ጦርነቱ እንዳይስፋፋ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ለማድረግ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ ጉብኝት ላይ ናቸው።
ትላንት እና ዛሬ፣ እስራኤልንና ዮርዳኖስን የጎበኙት ብሊንከን፣ ወደ ቃጣር፣ ግብጽ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስም ያቀናሉ፤ ተብሏል።
ሄንሪ ሪጅዌል እና ሲንዲ ሴይን ያጠናቀሩትን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም