በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሃማስ የአራት ታጋቾች አስከሬን ለእስራኤል አስረከበ


ሃማስ በዛሬው ዕለት ደቡባዊ ጋዛ ካን ዩኒስ ውስጥ ለእስራኤል ኃይሎች ያስረከባቸው አራት እስራኤላዊ ታጋቾችን አስከሬን የያዙ ሳጥኖች በቀይ መስቀል ተሽከርካሪዎች ወደ ቴላቪቭ ተጓጉዘዋል፤ ደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ ካን ዮኒስ፣ እአአ የካቲት 20/2025
ሃማስ በዛሬው ዕለት ደቡባዊ ጋዛ ካን ዩኒስ ውስጥ ለእስራኤል ኃይሎች ያስረከባቸው አራት እስራኤላዊ ታጋቾችን አስከሬን የያዙ ሳጥኖች በቀይ መስቀል ተሽከርካሪዎች ወደ ቴላቪቭ ተጓጉዘዋል፤ ደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ ካን ዮኒስ፣ እአአ የካቲት 20/2025

ሃማስ በዛሬው ዕለት ደቡባዊ ጋዛ ካን ዩኒስ ውስጥ ለእስራኤል ኃይሎች ያስረከባቸው አራት እስራኤላዊ ታጋቾችን አስከሬን የያዙ ሳጥኖች በቀይ መስቀል ተሽከርካሪዎች ወደ ቴላቪቭ ተጓጉዘዋል።

ባንዲራዎች እና ጹሑፎች የሰፈሩባቸው ጨርቆች በታዩበት መድረክ ሃማስ አስከሬኖቹን የተሸከሙትን አራት ጥቋቁር ሳጥኖች ባስረከበበት በዚህ ሥነ ስርዐት በብዙ መቶዎች የተቆጠሩ ሰዎች ተገኝተዋል።

አንዳንዶች ካነገቧቸው የተለያዩ መልዕክቶች ከሰፈረባቸው ጨርቆች አንዱ የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በጦር ወንጀለኝነት ይከሳል። የእስራኤል የአየር ጥቃት ለታጋቾቹ ሞት ‘ምክንያት ሆኗል’ ሲልም ይወነጅላል።

ቀይ መስቀል አራቱን የሬሳ ሳጥኖች ለእስራኤል ጦር ሠራዊት ማስረከቡን እና የሟቾቹን ማንነት ለማረጋገጥ አስከሬኖቹ ቴል አቪቭ ወደሚገኘው ብሔራዊ ልዩ ምርመራ ማዕከል መወሰዳቸውን የኔታንያሁ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

ለእስራኤል ተላልፈው የተሰጡት አስከሬኖች፤ በታገቱበት ወቅት የዘጠኝ ወር ዕድሜ የነበረውን ጨቅላ ልጃቸውን እና የታላቅ ወንድሙን የአራት ዓመቱን አርየል ቢባስን፤ የአባታቸውን የክፊር ቢባስን እና እንዲሁም የእናታቸውን ሺሪ ቢባስን ጨምሮ የአራቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ይገኙበታል።

የቢባስ ቤተሰብ አባላት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ጥቅምት 7 ቀን 2023 ዓ.ም ከኪቡትዝ ኒር ኦዝ በሃማስ ታጣቂዎች ታግተው ከተወሰዱት ውስጥ ናቸው።

የእገታውን ትዕይንት የሚያሳይ የቪዲዮ ምስል ሺሪ ቢባስ ሁለቱን ወንዶች ልጆቻቸውን በብርድ ልብስ ሲሸፋፍኑ እና በታጣቂዎች በኃይል እየተገፉ ሲወሰዱ ያሳያል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG