በሀማስ የሚመራው ጤና ሚኒስቴር 40ሺዎች ገድሏል ያለው የጋዛ ጦርነት የበለጠ እንዳይስፋፋ ለማድረግ የተኩስ አቁም ግፊት እየጨመረ ሲሆን ዛሬ ሐሙስ በካታር የሚደረገው ድርድር ቀጥሏል ።
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን እና የካታር ጠቅላይ ሚኒስትር ኢራንን፣ ሃማስን እና እስራኤልን የተኩስ አቁም ጥረቶችን ሊያደናቅፉ ከሚችሉ ርምጃዎች እንዲቆጠቡ አስጠንቅቀዋል።
የአሜሪካ፣ የካታር እና የግብፅ አስታራቂዎች እስራኤልን እና ሃማስን ለውይይት ጋብዘዋል፡፡
ግጭቱ ከሊባኖስ፣ ከየመን፣ ከኢራቅ እና ከሶሪያ ኢራን ጋር የተቆራኙ ቡድኖችን በመፍጠር በአጎራባች ሃገሮች ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡
በሊባኖስ የሚገኘው ሂዝቦላ ከእስራኤል ወታደሮች ጋር በየጊዜው ተኩስ ይለዋውጣል፡፡
ፈረንሣይ፣ ጀርመን እና ብሪታንያም አፋጣኝ እርቅ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበው ኢራን የአካባቢ ውጥረቶችን እንዳታባብስ አሳስበዋል። በጋዛ የአየር ድብደባዎች ጉዳት ማድረሱን አሁንም ቀጥለዋል በሃሙስ በደረሰው ጥቃት በጋዛ ከተማ አምስት ሰዎች ተገድለዋል።
የሲቪሎችና ተዋጊዎችን ሞት ለይቶ አላመለከተም የተባለው የጋዛ ጤና ሚኒስቴር ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ ብቻ 40 ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል፡፡
የእስካሁኑ የተኩስ አቁም ድርድር ጥረት ፍሬ ያላስገኘ ሲሆን የሰዎች እልቂት፣ መፈናቀልና፣ የመሠረተ ልማት ውድመትን ያስከተለ በመሆኑ በጋዛ ያለው ሁኔታ አሁንም አሳሳቢ እንደሆነ ቀጥሏል፡፡
መድረክ / ፎረም