በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል በሌባኖስ ላይ የምታደርሰው ጥቃት ጦርነቱ በቀጠናው እንዳይስፋፋ ስጋት ፈጥሯል


ፎቶ ፋይል፦ በሊባኖስና እስራኤል ድንበር አቅራቢያ በምትገኝ ኪያም ከተማ በእስራኤል የአየር ድብደባ የተፈፀመባቸው ቤቶች ወድመዋል፤ የሊባኖስ ከተማ ማርጃዩን፣ ሊባኖስ፣ እአአ ሰኔ 22/2024
ፎቶ ፋይል፦ በሊባኖስና እስራኤል ድንበር አቅራቢያ በምትገኝ ኪያም ከተማ በእስራኤል የአየር ድብደባ የተፈፀመባቸው ቤቶች ወድመዋል፤ የሊባኖስ ከተማ ማርጃዩን፣ ሊባኖስ፣ እአአ ሰኔ 22/2024

እስራኤል በኢራን በሚደገፈውና በሌባኖስ በሚገኘው ሄዝቦላ ላይ በማድረስ ላይ ያለችው ጥቃት ጦርነቱን በቀጠናው ሊያስፋፋና ኢራንንም ወደ ግጭቱ ሊከት እንደሚችል አሜሪካና የአውሮፓ ኅብረት ስጋታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው።

የአውሮፓ ኅብረት የውጪ ፖሊሲ ሃላፊ ጆሴፍ ቦረል ለክሰምበርግ ላይ ዛሬ ሰኞ ለጋዜጠኞ እንደተናገሩት፣ በጋዛ የሚካሄደው ጦነት ወደ ቀጠናው የመስፋፋት አደጋው በየቀኑ እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል።

“ጦርነቱ የሚስፋፋበት ዋዜማ ላይ እንገኛለን ብዬ አስባለሁ” ያሉት ቦሬል፣በጋዛ ሰብአዊ ርዳታ ማድረስ የማይቻልበት ደረጃ እንደደረሰ ተናግረዋል። የተኩስ አቁም ላይ መድረስ የሰብአዊ ርዳታ ፍሰትን ለማስቻል እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል።

የቦሬል አስተያየት የመጣው፣ አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ወታደራዊ ባለሥልጣን፣ እስራኤል በሌባኖስ ላይ የምታካሂደው ጥቃት፣ ሄዝቦላን ለመደገፍ ስትል ኢራን እንድትገባበት ሊያደርግ እንደሚችል ባስጠነቀቁ በሰዓታት ውስጥ ነው።

የአሜሪካ የኤታማዦር ሹሞች ኃላፊና የአየር ኃይል አዛዥ ጀኔራል ሲ ኪው ብራውን ለሪፖርተሮች እንደገለጹት፣ ኢራን ሄዝቦላን ወደ መደገፉ ልታዘነብል ትችላለች። ሄዝቦላ ከሐማስ የተሻለ አቅርቦት እንዳለው ጀኔራሉ ጠቁመዋል።

በጋዛ ከሐማስ ጋራ የሚካሄደው ጦርነት ከባዱ ምዕራፍ “በቅርቡ” ያበቃል ሲሉ ትላንት እሁድ የተናገሩት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጀሚን ኔታንያሁ፣ እስራኤል ጦሯን ከሌባኖስ ጋራ ወደሚዋሰነው ድንበር ልታሻግር እንደምትችል ገልጸዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG