በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጋዛ ተኩስ አቁምን ዳር ለማድረስ ድርድሩ ቀጥሏል


የተፈናቀለች ፍልስጤማዊ እንደ ጊዜያዊ መጠለያ በሚያገለግለው የስደተኞች ካምፕ ውስጥ በማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥ በአል-ቡሬጅ የስደተኞች ካምፕ እአአ ሰኔ 12/2024
የተፈናቀለች ፍልስጤማዊ እንደ ጊዜያዊ መጠለያ በሚያገለግለው የስደተኞች ካምፕ ውስጥ በማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥ በአል-ቡሬጅ የስደተኞች ካምፕ እአአ ሰኔ 12/2024

ዩናይትድ ስቴትስ ሀማስ በርከት ያሉ ያሉ የማሻሻያ ሃሳቦችን ማቅረቡን ተከትሎ የጋዛ ተኩስ አቁም ሃሳቡን ዳር ለማድረስ ጥረት ማድረጓን ቀጥላለች፡፡

የኋይት ሐውስ የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ ጄክ ሰለቫን ዛሬ ሐሙስ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ሃማስ ያቀረባቸው አንዳንዶቹ ጥያቄዎች “መለስተኛ እና ጥቃቅን “ ስለሆኑ ሊሠራባቸው የሚቻሉ ናቸው ብለዋል፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በዝርዝር ካቀረቡዋቸውም ሆነ በተመድ የጸጥታ ምክር ቤት ከጸደቁት ማዕቀፎች ጋር የሚጣጣሙ አይደሉም ሲሉም አክለዋል፡፡ ድርድሮቹ በግብጽ እና በካታር ባለስልጣናት አማካይነት በተዘዋዋሪ የሚካሄድ እንደመሆኑ ጊዜ እንደሚወስድ እንዲጤን ጄክ ሰለቫን አሳስበዋል፡፡

“እኛ ከካታር እና ከግብጽ ጋር እንሠራለን፡፡ ካታር እና ግብጽ ደግሞ ከሐማስ ጋር ይሠራሉ፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ ደግሞ ከእስራኤል ጋር ትሠራለች፡፡ ዓላማችን በተቻለ ፍጥነት ለማጠናቅቅ ነው ብለዋል” ጄክ ሰለቫን፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤል የጦር ኅይል በመላዋ ጋዛ ባሉ አርባ አምስት ዒላማዎች ላይ የአየር ጥቃት ማካሄዱን አስታውቋል፡፡ በተጨማሪም በደቡባዊ ጋዛ ራፋህ አካባቢ በምድር ጦር እና በአየር ጥቃት ማድረሱ በማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥም ጥቃቶች ማካሄዱን ገልጿል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG