የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ዛሬ ማክሰኞ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በጋዛ ለታቀደው የባለብዙ እርከኖች የተኩስ አቁም ስምምነት ቁርጠኝነታቸውን ማረጋገጣቸውን አመልክተው ‘አሁን የሚጠበቀው የሃማስ ስምምነት ብቻ ነው’ ብለዋል። ብሊንከን ቴል አቪቭ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት አስተያየት "ከአንድ ድምጽ በስተቀር የሁሉም ድምጽ ተሰምቷል። ያም ድምጽ የሃማስ ነው” ብለዋል።
ስምንት ወራት የዘለቀው ጦርነት እንዲያበቃ ለማድረግ የተያዘው አለማቀፍ ግፊት እያየለ በመጣበት፣ ‘የተኩስ አቁሙን ሃሳብ መቀበል አለበት’ ሲሉም ብሊንከን ትላንት ካይሮ ላይ ሃማስን አሳስበዋል።
መድረክ / ፎረም