በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋዛው ጦርነት የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥረቱ ቀጥሏል


የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን ዛሬ ዓርብ በቴል አቪቭ
የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን ዛሬ ዓርብ በቴል አቪቭ

በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተኩስ አቁም እንዲደረግ ለማስቻል የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን ዛሬ ዓርብ በቴል አቪቭ ሲገኙ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ም/ቤት በበኩሉ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ በሚጠይቀውና በአሜሪካ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ድምፅ ለመስጠት በዝግጅት ላይ ነው።

ብሊንከን ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔተንያሁ ጋራ ተገናኝተው ከተነጋገሩ በኋላ፣ በጦር ካቢኔው ስብሰባ ላይም ተገኝተዋል። ብሊንከን በስብሰባው እስራኤል በደቡብ ጋዛ በምትገኘው የራፋ ከተማ ላይ ወታደራዊ ጥቃት እንዳትፈጽም ለማሳመን ሞክረዋል ተብሏል።

እስራኤል በራፋ ላይ ጥቃት ከሰነዘረች የሰብአዊ ቀውሱን ያባብሰዋል የሚል ፍራቻ እያየለ መጥቷል።

በራፋ ላይ ያቀደችው ጥቃት፣ በአሜሪካ በሽብርተኝነት የተፈረጀውን ሐማስ ለማጥፋት የያዘችውን ግብ የሚያሳካ ነው ስትል እስራኤል ትከራከራለች፡፡

የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና ታጋቾችም እንዲለቀቁ የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ አሜሪካ ዛሬ ዓርብ በፀጥታው ም/ቤት ድምፅ እንዲሰጥበት እንደምታቀርብ፣ በተመድ የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ለስድስት ሳምንታት የሚቆይ የተኩስ አቁም እንዲኖር፣ በሐማስ የታገቱ እንዲለቀቁ እና በምትኩም በእስራኤል የተያዙ ፍልስጤማውያን እስረኞች ነጻ እንዲወጡ የሚያስችል ሃሳብ ተቀባይነት እንዲያገኝ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ሲደራደሩ ሰንብተዋል።

በዚሁ በእስራኤል እና ሐማስ ጉዳይ ላይ ለመምከር አንተኒ ብሊንከን ትላንት ሐሙስ በግብጽ ቆይታ ማድረጋቸው ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG