በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

‘በጋዛው ጦርነት የሟቾች ቁጥር ከ26 ሺህ አለፈ' - የጋዛ ጤና ሚኒስቴር


ፍልስጤማዊት ሴት ከቁስለኛ ልጇ አጠገብ ተቀምጣ
ፍልስጤማዊት ሴት ከቁስለኛ ልጇ አጠገብ ተቀምጣ

ሦስት ወራት ባስቆጠረው ጦርነት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ‘ከ26 ሺህ በላይ ሲደርስ፤ ሌሎች ከ64 ሺህ 400 የሚበልጡ መቁሰላቸውን የጋዛ የጤና ሚንስቴር ባለስልጣናት ተናገሩ።

ሚኒስቴሩ ዛሬ ዓርብ ማለዳ በሰጠው መግለጫ፡ "ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በእስራኤል የአየር ድብደባ 183 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን እና ተጨማሪ 377 ሰዎች መቁሰላቸውን" አመልክቷል። በተጨማሪም፡ ማዕከላዊ ጋዛ ውስጥ በሚገኘው የአል ኑሴይራት የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ፡ ባለ አንድ ቤት ላይ ‘ሌሊቱን በተፈጸመ የእስራኤል የአየር ጥቃት ስድስት ሰዎች ተገድለዋል’ ሲሉ ባለስልጣናቱ አመልክተዋል።

በሌላ በኩል፡ ባለፈው ሐሙስ ጋዛ ውስጥ ሰብዓዊ እርዳታ በመጠባበቅ ላይ ከነበሩ ፍልስጤማውያን ውስጥ 20 ሰዎችን የገደለውን እና ሌሎች 150 ሰዎችን ያቆሰለውን ጥቃት እየመረመረ መሆኑን የእስራኤል የጦር ሠራዊት አስታውቋል።

በተመሳሳይ ደቡባዊ ጋዛ፡ ካን ዩኒስ በሚገኝ የተባበሩት መንግሥታት የማሰልጠኛ ማዕከል ላይ ባለፈው ረቡዕ በደረሰው ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 12 መድረሱን እና ከ75 በላይ ሌሎች መቁሰላቸውን በተባበሩት መንግሥታት የፍልስጤም የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት ከፍተኛ ባለስልጣን ቶማስ ዋይት ተናግረዋል።

ምንም እንኳን የመንግሥታቱ ድርጅት ቀደም ሲል በታንክ ጥይት መመታቱን፤ ጋዛ ውስጥ በትልቅነቷ ሁለተኛ ከሆነችው ከተማ ውስጥ ታንኮች ያለው ብቸኛ ኃይልም የእስራኤል ጦር መሆኑን ቢናገርም፤ ለጥቃቱ ግን እስራኤልን በቀጥታ ተጠያቂ አላደረገም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG