በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል እና ሐማስ ጦርነት ተፋፍሞ ቀጥሏል


የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ነታንያሁ
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ነታንያሁ

በሂዝቦላ የተፈጸመ የሮኬት ጥቃትን ተከትሎ፣ በእስራኤል እና በሌባኖስ ድንበር ላይ ከባድ ፍንዳታ ተሰምቷል ተብሏል።

በሁለቱ አገራት ድንበር ላይ የሚገኘው አስፈሪ ተራራማ አካባቢ በጭስ ሲታጠን፣ ከባድ ፍንዳታም ሲሠማበት ውሏል።

የእስራኤል ቻናል 13 እንደዘገበው፣ በሂዝቦላ ተዋጊዎች የተፈጸመ ነው በተባለ የሚሳኤል ጥቃት፣ በሰሜን እስራኤል አንድ ሰው ተገድሏል።

በአካባቢው ያለው የአምቡላንስ አገልግሎት፣ ከሌባኖስ ጋር በሚያዋስነው ድንበር አካባቢ አንድ የ60 ዓመት ነዋሪ እንደተገደለ አስታውቋል።

የእስራኤል ኃይሎች እና የሐማስ ተዋጊዎች ዛሬም ከፍተኛ ውጊያ ሲያደርጉ መዋላቸው ታውቋል።

በሰሜን በሚገኘው ጋዛ ከተማ እና እንዲሁም በቅርቡ የጦር አውድማ በሆነው በደቡብ በሚገኘው ካን ዩኒስ አካባቢ ውጊያው ተፋፍሞ መቀጠሉ ተሰምቷል። ሲቪሎች ከውጊያ ከለላ የሚያገኙበት ቦታ እየጠበበ መጥቷል ተብሏል።

የተመድ የሰብዓዊ ሥራ የተስተጓጎለ ሲሆን፣ ነገሮች አስከፊ እየሆኑ እንደመጡ ማስጠንቀቂያዎች ተሰጥተዋል።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ነታንያሁ እንዳስታወቁት፣ በጋዛ የሐማስ አለቃ የሆነው ያህያ ሲንዋር ወደሚገኝበት አካባቢ ኃይላቸው እየተቃረበ ሲሆን፣ የግለሰቡ መገኘት የግዜ ጉዳይ ነው ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG