በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሐማስ የእስራኤላዊዋን አስከሬን የማይመልስ ከሆነ “ዋጋ ይከፍላል” ሲሉ ኔታንያሁ አስጠነቀቁ


ይህ ፖስተር ከባለቤቷ እና ከሁለት ወጣት ልጆቿ ጋር የታገተችውን ሺሪ ቢባስን ምስል ያሳያል፤ እአአ ጥቅምት 7/2023
ይህ ፖስተር ከባለቤቷ እና ከሁለት ወጣት ልጆቿ ጋር የታገተችውን ሺሪ ቢባስን ምስል ያሳያል፤ እአአ ጥቅምት 7/2023

ሐማስ በሰላም ስምምነቱ መሠረት ሺሪ ቢባስ የተባለችውን እስራኤላዊ እናት አስከሬን የማይመልስ ከሆነ “ዋጋ ይከፍላል” ሲሉ የእስራኤሉ ጠቅላይ ምኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ዛሬ ዓርብ አስጠንቅቀዋል።

“ሺሪን ጨምሮ በሕይወት ያሉም ሆነ የሌሉ እስራኤላውያንን ለማስመለስ በቁርጠኝነት ርምጃ እንወስዳለን። ለዚህ ጨካኝና ሰይጣናዊ ለሆነ እንዲሁም ስምምነቱን ለጣሰ ተግባር ሐማስ ሙሉ ዋጋውን እንዲከፍል እናደርጋለን” ሲሉ ኔታንያሁ በቪዲዮ ባስተላልፉት መልዕክት አስታውቀዋል።

ሐማስ በትላንትናው ዕለት አራት ታጋቾችን የለቀቀ ሲሆን እነዚህም በታገተበት ወቅት የዘጠኝ ወር ሕፃን የነበረው ክፊር ቢባስ፣ የአራት ዓመት ወንድሙ አሪየል ቢባስ ይገኙበታል። የእናታቸው ሺሪ ቢባስ ነው ተብሎ የተመለሰው አስከሬን ግን የእርሷ እንዳልሆነ የእስራኤል ሠራዊት ዛሬ ዓርብ አስታውቋል።

“ሐማስ አባትና እናትን እንዲሁም ሁለት ልጆቻቸውን ማገቱ ብቻ ሳይሆን፣ በአሳዛኝ ሁኔታ የእናቷ አስከሬን ነው በሚል የአንድ የጋዛ ነዋሪን ሴት አስከሬን ልኳል” ሲሉ አክለዋል ጠቅላይ ምኒስትሩ።

ሐማስ በበኩሉ ሽሪ ቢባስ ተይዛ በነበረችበት ስፍራ እስራኤል ባደረሰችው የአየር ጥቃት በፍርስራሹ ውስጥ አስከሬኗ ከሌላ አስከሬን ጋራ ተነካክቷል ሊሆን እንደሚችል አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG