በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል በጋዛ በተባበሩት መንግሥታት የሚተዳደረውን ትምህር ቤት ደበደበች


ኑሴይራት የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጤም ስደተኞች ተቋም
ኑሴይራት የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጤም ስደተኞች ተቋም

የእስራኤል ጦር ዛሬ ሐሙስ በማዕከላዊ ጋዛ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ትምህርት ቤት የአየር ድብደባ ፈጽሟል፣ የፍልስጤም የጤና ባለሥልጣናት በድብደባው በትንሹ 33 ሰዎች መሞታቸውን ገልጸዋል።

የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት፣ “እኤአ ጥቅምት 7 በእስራኤል ላይ በተፈጸመው ጥቃት የተሳተፉ የሃማስ ተዋጊዎች ትምህርት ቤቱን እንደ መጠለያ እና "የሽብር ትዕዛዝ ማስተላለፊያነት" ይጠቀሙበት ነበር” ብሏል።

የሃማስ የሚዲያ ቢሮ የእስራኤልን መግለጫ ውድቅ አድርጓል፡፡ የእስራኤል ወታደሮች በተፈናቀሉ ሰዎች ላይ “አሰቃቂ ወንጀል” መፈጸማቸውን ገልጾ ከሟቾች መካከል 23 ሴቶች እና ህጻናት እንደሚገኙበት ቢሮው ገልጿል።

የእስራኤል ወታደራዊ ቃል አቀባይ ሌተናል ኮሎኔል ፒተር ለርነር ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት “እስራኤል በሲቪሎች ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ አታውቅም” ብለዋል፡፡

ጥቃቱ የተፈፀመው ኑሴይራት በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጤም ስደተኞች ተቋም በሚመራው ትምህርት ቤት ላይ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በጋዛ ለስድስት ሳምንታት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነትን በይፋ ከገለፁ ከአንድ ሳምንት ገደማ በኋላ አሜሪካ እና ሌሎች 16 ሀገራት ስምምነቱን እንደሚደግፉ በመግለጽ ዛሬ ሐሙስ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።

“ሀማስ ይህንን ስምምነት ተቀብሎ እንዲዘጋ እና ዜጎቻችንን ነጻ የማውጣት ሂደቱን እንዲጀምር እንጠይቃለን።” ያለው መግለጫው "እስራኤል በዚህ ስምምነት ወደፊት ለመራመድ ዝግጁ ነች" ብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG