በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተኩስ አቁም ጥረቱ በቀጠለበት እስራኤል ካን ዮኒስን ደበደበች


በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ ካን ዮኒስ በሚገኘው የአውሮፓውያን ሆስፒታል አቅራቢያ በቦምብ ድብደባው የተገደሉ ፍልስጤማውያን፣ ዘመዶቻቸው በሀዘን ሲያለቅሱ ይታያል፤ እአአ መጋቢት 5/2024
በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ ካን ዮኒስ በሚገኘው የአውሮፓውያን ሆስፒታል አቅራቢያ በቦምብ ድብደባው የተገደሉ ፍልስጤማውያን፣ ዘመዶቻቸው በሀዘን ሲያለቅሱ ይታያል፤ እአአ መጋቢት 5/2024

የእስራኤል ጦር ዛሬ ማክሰኞ በደቡባዊ ጋዛ ካን ዮኒስን ላይ ወታደራዊ አሰሳ ማድረጉን ሲያስታውቅ፤ የፍልስጤም ባለስልጣናት በበኩላቸው በእስራኤል የአየር ድብደባ 17 ሰዎችን መገደላቸውን አመልክተዋል። የአየር ድብደባው የተፈጸመው ‘ሃማድ’ ከተባለው መንደር ውስጥ ከአንድ የአውሮፓውያን ሆስፒታል አቅራቢያ መሆኑን ባለስልጣናቱ ተናግረዋል።

የእስራኤል ጦር ሠራዊት በበኩሉ፡ በሃማድ የፈጸመው ወታደራዊ ጥቃት ‘አሸባሪ ቡድኑ የሚጠቀምባቸውን መሠረተ ልማቶች ኢላማ ያደረገ ሲሆን፤ ‘ከሰላማዊ ሰዎች መሃል ተሸሽገው የነበሩ በርካታ የሃማስ እና የእስላማዊው ጂሃድ ተዋጊዎችን በቁጥጥር ሥር አውያለሁ’ ብሏል።

የጋዛው ውጊያ የቀጠለው ግብፅ ውስጥ እየተካሄዱ ያሉትን ንግግሮች ጨምሮ፡ ከአንዳች የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ የተያዙት ብርቱ ጥረቶች በቀጠሉበት በዚህ ወቅት ነው።

ታጣቂዎች ጋዛ ላይ ይዘዋቸው የሚገኙትን ታጋቾች ስም ዝርዝር ለመስጠት ‘አሁንም ፍቃደኛ አልሆነም’ ስትል ሃማስን የወነጀለችው እስራኤል በካይሮው ድርድር ላይ አልተገኘችም።

‘ስምምነቱ እንዳይደረስ ተጠያቂው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ናቸው” ያሉ አንድ ከፍተኛ የሃማስ ባለስልጣን በበኩላቸው፡ ዛሬ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፡ "አሁን ጉዳዩ፡ የእስራኤል አጋር ከሆነችው ዩናይትድ ስቴትስ እጅ ነው ያለው። ግፊት ማድረግም አለባት’ ብለዋል።

በሌላ ዜና የዩናይትድ ስቴትሷ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ ትላንት ሰኞ የተኩስ አቁም ጥረቱን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት፡ ‘ሃማስ ታጋቾች መልቀቅ፡ ለስድስት ሳምንታት የሚዘልቅ የተኩስ አቁም በአፋጣኝ እውን የሚያደርገውን እና በመላው ጋዛ የሚደርሰው የሰብአዊ እርዳታ መጠንም እንዲጨምር የሚያስችለውን የስምምነቱን ውሎች መቀበል አለበት’ ሲሉ አሳስበዋል።

ሃሪስ የእስራኤል የጦርነት ጊዜ ካቢኔ አባል የሆኑትን ቤኒ ጋንትዝን በዋይት ሀውስ ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች ጭምር የታገቱበትን የመስከረም 26ቱን የሃማስ የሽብር ጥቃትም አውግዘዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG