በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለሐማስ ታጋቾች መድሃኒት ሊላክ ነው


ዕርዳታ የጫኑ መኪናዎች በራፋህ
ዕርዳታ የጫኑ መኪናዎች በራፋህ

በፈረንሣይ እና በካጣር አሸማጋይነት በተደረሰ ስምምነት መሠረት፣ በሐማስ ቁጥጥር ሥር ላሉ ታጋቾች መድሃኒት ሊላክ እንደሆነ ተሰምቷል።

መድሃኒቶቾቹ የጠና ሕመም ላለባቸው 45 ለሚሆኑት ታጋቾች እንደሚላክና በዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል በኩል እንዲደርሳቸው እንደሚደረግ ፈረንሣይ አስታውቃለች፡፡

ካጣር በበኩሏ እንደገለጸችው፣ ስምምነቱ በተጨማሪም በጋዛ ሰርጥ ለሚገኙ ፍልስጤማውያን ሲቪሎች መድሃኒት እና ሌሎች ሰብዓዊ ርዳታዎችን ለማድረስ ያስችላል።

እ.አ.አ ጥቅምት 7 ቀን ሐማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት ሲሰነዝር 1ሺሕ 200 ሰዎችን ገድሎ፣ 240 ሰዎችን አግቶ ወስዷል። ጥቃቱን ተከትሎ እስራኤል ሐማስን ለመደምሰስ ዘመቻ በማድረግ ላይ ነች፡፡

ባለፈው አንድ ቀን ውስጥ ብቻ እስራኤል ባደረሰችው ጥቃት 163 ሰዎች ሲገደሉ፣ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 24 ሺሕ 448 መድረሱን በጋዛ የሚገኘው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ከዚህ በተጨማሪም በዌስት ባንክ እስራኤል በከፈተችው ጥቃት 350 ፍልስጤማውያን እንደተገደሉ ታውቋል።

የዌስት ባንክ ከተማ በሆነችው ናብለስ ዛሬ ባደረሰው የአየር ጥቃት አንድ ከፍተኛ ፍልስጤማዊ ተዋጊ መገደሉን የእስራኤል ሰራዊት አስታውቋል። አህመድ አብዱላ አቡ ሻላል የተባለው ግለሰብ በእየሩሳሌም በሚገኙ እስራኤላውያን ላይ ለደረሱ በርካታ ጥቃቶች ተጠያቂ ነው ሲል ሠራዊቱ ከሷል።

የሕክምና ባለሙያዎች የአየር ጥቃት በደረሰበት አካባቢ ገብቶተው ተጎጂዎችን እንዳያነሱ በእስራኤል ኃይሎች እንደተከለከሉ የፍልስጤማውያን ቀይ ጨረቃ ማኅበር አስታውቋል።

በተጨማሪም እስራኤል በዌስት ባንክ ቱልካርም በተሰኘ የፍልሰተኞች መጠለያ ላይ ድብደባ ማድረጓን ተከትሎ፣ አምቡላንሶች እንዳይገቡ የእስራኤል ኃይሎች መከልከላቸውን ማኅበሩ ገልጿል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG