ሁለተኛ ሳምንቱን የያዘው የእስራኤል እና የሐማስ ግጭት፣ የተባባሰው የጋዛ ሰብአዊ ቀውስ፣ ተስፋ የተጣለበት “ሕይወት አድን” ርዳታ እና እስራኤል ለተቀናጀ የምድር ውጊያ ጦሯን በጋዛ ዙሪያ በተጠንቀቅ ያቆመችበት ኹኔታ እያነጋገሩ ነው።
ይህንኑ አስመልክቶ፣ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ተጉዘው የተመለሱት የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ የአገራቸውን አቋም እና በሌሎችም ተዛማጅ ርእሶች፣ ትላንት ኀሙስ ምሽት፣ ለአሜሪካ ሕዝብ ንግግር አሰምተዋል።
የንግግራቸውን ይዘት እንዲተነትኑ፣ በኒው ዮርኩ ስቶኒ ብሩክ ዩኒቨርሲቲ የዘመናዊ ታሪክ ፕሮፌሰር ሽመልስ ቦንሳን ጋብዘናል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም