በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል በጋዛ ላይ የአየር ጥቃቷን ቀጥላለች


በደቡብ ጋዛ በደረሰ አየር ጥቃት በህይወት የተረፉ ካሉ ፍለጋ እያደረጉ፤ ካን ዮኒስ እስራኤል፣ አአአ ጥቅምት 19/2023
በደቡብ ጋዛ በደረሰ አየር ጥቃት በህይወት የተረፉ ካሉ ፍለጋ እያደረጉ፤ ካን ዮኒስ እስራኤል፣ አአአ ጥቅምት 19/2023

እስራኤል፣ በደቡብ ጋዛ በካን ዮኒስ በሚገኝ አንድ መኖሪያ ቤት ላይ ከአየር ባደረሰችው ጥቃት፣ ሕፃናትን ጨምሮ አራት ፍልስጥኤማውያን እንደተገደሉ፣ ሮይተርስ የሐማስ ሚዲያን ጠቅሶ ዘግቧል።

በአየር ጥቃቱ፣ በርካቶች እንደቆሰሉም ታውቋል።

ግጭቱ ከጀመረ አንስቶ፣ 3ሺሕ478 ፍልስጥኤማውያን እንደተገደሉና 12ሺሕ65 ደግሞ እንደቆሰሉ፣ የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

እስራኤል፣ ዛሬ ኀሙስ፣ ከጥቃት ነጻ ነው ብላ ባስታወቀችው ደቡብ ጋዛ፣ የአየር ድብደባዋን እንደቀጠለች ታውቋል። በዚኽም ምክንያት፣ በቦታው የሚኖሩ ሁለት ሚሊዮን ፍልስጥኤማውያን፣ ደኅንነታቸው የሚጠበቅበት ሥፍራ እንደሌለና ስጋት ላይ እንደወደቁ ተመልክቷል።

የአየር ጥቃቱ የተፈጸመው፣ ግብጽ ከደቡብ ጋዛ ጋራ ባላት ደንበር በኩል፣ የተወሰነ የሰብአዊ ርዳታ ወደ ጋዛ እንድታስገባ፣ እስራኤል መስማማቷን ከገለጸችም በኋላ ነው።

ጋዛ፣ ላለፉት 11 ቀናት በእስራኤል ኀይሎች ዙሪያ ከበባ ውስጥ ትገኛለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG