በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንድ ኤርትራዊ ፍልሰተኛ በእሥራኤል ፖሊስ በስህተት ተተኩሶበት መሞቱ ተገለጸ


ኤሪትራዊው ፍልሰተኛ የሞተው በስህተት በተተኮሰበት ጥይት ሲሆን፤ የተኩሱ ዒላማ ግን፣ አንድ የእሥራኤል ወታደር በመግደል ሌሎች 10 ሰዎችን አቁስሎ በኦቶቡስ ያመለጠ ተጠርጣሪን ለመግደል ያነጣጠረ እንደነበር ታውቋል።

ኤሪትራዊው ፍልሰተኛ የሞተው በስህተት በተተኮሰበት ጥይት ሲሆን፤ የተኩሱ ዒላማ ግን፣ አንድ የእሥራኤል ወታደር በመግደል ሌሎች 10 ሰዎችን አቁስሎ በአቶቡስ ያመለጠ ተጠርጣሪን ለመግደል ያነጣጠረ እንደነበር ታውቋል።

በፖሊስ መግለጫ መሠረት፣ መኰንኑ ትናንት እሑድ በስህተት የገደለው ኤሪትራዊ የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ድረ-ገጾች ሙሉ ሃብቶም ዘርኦም በሚለው ስም ቢጠሩትም፣ ጓደኞቹ ለአሜሪካ ድምጽ እንዳስታወቁት ሙሉ ስሙ ሃብቶም ወልደሚካኤል ነው።

ኤሪትራዊው ወጣት በ፳ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ጥገኝነት ጠያቂ እንደነበርም፣ የአካባቢው ዜና አውታሮች ዘግበዋል።

የእሥራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንዣሚን ናታንኛሁ በተናገሩት ቃል፣ ማንም ቢሆን ከህግ በላይ ስላልሆነ ህግን በራሱ ቁጥጥር ስር በማድረግ እንዳይተገብር አስጠንቅቀዋል።

የእሥራኤል የደኅንነት ባለሥልጣናት ዛሬ ሰኞ ይፋ እንዳደረጉት፣ ጥቃቱን የፈጸመው ከወታደራዊ ሙያ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌለው የ21 ዓመቱ መሓመድ አል-አካቢ የተባለ ነው።

አል-አካቢ በከፈተው ተኩስ የ19 ዓመቱን እሥራኤላዊ ወታደር ከገደለ በኋላ፣ ፖሊሶች በተደጋጋሚ በመተኮስ ሊገድሉት ችለዋል።

በዚህ ሳምንት ውስጥ የእሥራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ናታንኛሁንና የፍልስጤማውያኑን ፕሬዚደንት ሞሓመድ ኣባስን በተናጠል ለማግኘት በዝግጅት ላይ የሚገኙት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ዛሬ ሰኞ ባስተላለፉት ማሳሰቢያ፣ «ተረጋጉ» ብለዋል።

አመጽ ቆሞ፣ መረጋጋት ሰፍኖ ማየት እንፈልጋለን፣ ይህ ደግሞ እሥራኤል ውስጥም ሆነ በክልሉ የሚገኙ ሕዝቦች ሁሉ ፍላጎት ነው
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ

«እሥራኤል ደግሞ፣ በድንገት ከሚደርስባት ማንኛውም አደጋ እራሷን የመከላከል መብት አላት» ሲሉ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ አክለውበታል።

ዘገባውን የተያያዘውን የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳመጡ።

አንድ ኤርትራዊ ፍልሰተኛ በእሥራኤል ፖሊስ ተተኩሶበት መሞቱ ተገለጸ /ርዝመት - 1ደ22ሰ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:21 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG