የእስራኤል የጦር ኃይል በጎርጎርሳዊያኑ ጥቅምት ሰባት ሓማስ ባደረሰው ጥቃት ላይ በቪዲዮ ምስል የሚታይ የቡድኑን ታጣቂ መግደሉን አስታወቀ፡፡ የጦር ኃይል የእስራኤል የጦር ኃይል ዛሬ ማክሰኞ እንዳስታወቀው የተገደለው የሐማስ ታጣቂ አባታቸው በቦንብ ጥቃት የተገደለባቸው ሁለት የቆሰሉ ህጻናት ፊት ለስላሳ መጠጥ ሲጠጣ በቪዲዮ ምስሉ በሰፊው የሚታየው ነው፡፡
የእስራኤል መከላከያ ኃይል ታጣቂው በጥቅምቱ ጥቃት ወቅት በአየር መብረሪያ ፓራግላይደር ወደ ኔቲቭ ኻሳራ መንደር ቀዝፎ የወረደው አህመድ ፎዚ ዋዲያ መሆኑን ተናግሯል።
ዋዲያ ቅዳሜ ዕለት በጋዛ ከተማ በእስራኤል የአየር ጥቃት ከተገደሉት ስምንት ታጣቂዎች መካከል አንዱ መሆኑንም የጦር ኃይሉ ጨምሮ አስታወቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ፅህፈት ቤት ዛሬ ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ "ብሪታኒያ የጦር መሳሪያ ብትሰጥም ባትሰጥም ከሀማስ ጋር በምናደርገው ጦርነት እናሸንፋለን" ብሏል፡፡ የእንግሊዝ መንግስት እስራኤል በሚላኩላት መሣሪያዎች ጋዛ ላይ አጠቃቀሟ ስላሳሰበው አንዳንዶቹን የጦር መሳሪያዎች እንደማይልክ አስታውቋል።
የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴቪድ ላሚ " አንዳንዶቹ የጦር መሳሪያዎችን "በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ህግ ላይ ከባድ ጥሰት ለመፈጸም ወይም ለማመቻቸት ሊውሉ እንደሚችሉ ግልጽ ስጋት አለ" ብለዋል፡፡
መድረክ / ፎረም