በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍልስጤማውያን "በጋዛ ት/ቤት የተጠለሉ 27 ሰዎች በእስራኤል ጥቃት ተገድለዋል" አሉ


ፍልስጤማውያን በማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥ ዲር አል ባላህ በሚገኝ ትምህርት ቤት በእስራኤል በደረሰ ጥቃት የተገደሉትን የዘመዶቻቸውን አስከሬን እየፈለጉ እአአ ጥቅምት 10/2024
ፍልስጤማውያን በማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥ ዲር አል ባላህ በሚገኝ ትምህርት ቤት በእስራኤል በደረሰ ጥቃት የተገደሉትን የዘመዶቻቸውን አስከሬን እየፈለጉ እአአ ጥቅምት 10/2024

እስራኤል ጋዛ ውስጥ ፍልስጤማውያን ተፈናቃዮች በተጠለሉበት ትምህርት ቤት ላይ ዛሬ ሐሙስ በፈጸመችው የአየር ጥቃት 27 ሰዎች ተገድለዋል" ሲሉ ፍልስጤማውያን ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡

እስራኤል "ጥቃቱ ትምህርት ቤቱ ውስጥ የመሸገውን የታጣቂዎች የዕዝ ማዕከል ኢላማ ያደረገ ነው" ብላለች፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት "እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ በሚገኘው የሰላም አስከባሪ ይዞታ ላይ በመተኮስ ሁለት አባላትን አቁስላለች" ሲል ከሷታል፡፡

እስራኤል ክስተቱን እየመረመረች መሆኑን አስታውቃለች፡፡

የእስራኤል ጦር ቀደም ሲል ከሊባኖስ ለተተኮሰው የሚሳይል ጥቃት ምላሽ ለመስጠት አህመድ ሙስጠፋ አል ሃጅ አሊ እና መሀመድ አሊ ሃምዳን የተባሉ ሁለት የሂዝቦላህ አዛዦችን የገደለበትን የአየር ድብደባ መፈጸሙን አስታውቋል፡፡

ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ጋር ትላንት ረቡዕ በስልክ የተነጋገሩት የይናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን፣ ለእስራኤል “የማይናወጥ ጠንካራ” ድጋፋቸውን በድጋሚ ያረጋገጡ ሲሆን በሃማስ የተያዙ ታጋቾችን ለማስፈታት በሚደረገው ጥረት ላይ ተወያይተዋል።

ሁለቱ መሪዎቹ ቴህራን እኤአ በጥቅምት 1 ቀን 200 ባሊስቲክ ሚሳይሎችን ወደ እስራኤል መተኮሷን ተከትሎ ጦርነቱ ስላስከተለው ሰብአዊ ተፅዕኖ እና እስራኤል ለኢራን ልትሰጥ ስለምትችለው ምላሽ ተወያይተዋል።

ባይደን እና ኔታኒያሁ ያደረጉት የስልክ ውይይት እአአ ከነሀሴ 21 ወዲህ የመጀመሪያቸው ነው፡፡ በስልክ ውይይቱ ምክትል ፕሬዚደንት ከማላ ሃሪስም መሳተፋቸውን ኋይት ሐውስ አስታውቋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG