በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል በጋዛ የምድር ማጥቃቷን አስፋፍታለች


እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ በካን ዩኒስ የፈፀመችውን ጥቃት ተከትሎ ፍልስጤማውያን ጉዳት የደረሰበት ሕንፃ አካባቢ ቆመው ይመለከታሉ፤ እአአ ጥቅምት 30/2023
እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ በካን ዩኒስ የፈፀመችውን ጥቃት ተከትሎ ፍልስጤማውያን ጉዳት የደረሰበት ሕንፃ አካባቢ ቆመው ይመለከታሉ፤ እአአ ጥቅምት 30/2023

እስራኤል፣ ዛሬ ሰኞ፣ ወታደሮቿንና ታንኮቿን ወደ ሰሜን ጋዛ በማስገባት በከበባ ውስጥ ባስገባቻት ሰርጥ የምታካሒደውን የምድር ወታደራዊ ማጥቃት አስፋፍታለች፡፡

አንድ የእስራኤል ታንክ እና አፈር ቆፋሪ ቡልዶዘር፣ የጋዛን ደቡብ እና ሰሜን ክፍል የሚያገናኘውን ዋና አውራ ጎዳና ዘግቶ የሚያሳይ ምስል ማግኘቱን፣ የአሶሺዬትድ ፕረስ ዜና ወኪል አስታውቋል። መንገዱ፣ ከምታካሒደው የምድር ማጥቃት ፍልስጥኤማውያኑ ራሳቸውን ለመጠበቅ እንዲጠቀሙበት እስራኤል ያስታወቀችበት እንደነበር ዘግቧል።

የእስራኤል አየር ኃይል በበኩሉ፣ በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ 600 የሐማስ ዒላማዎችን እንደመታች አስታውቋል። በተጨማሪም፣ በሶሪያ እና በሊባኖስ የሚገኙ ዒላማዎችንም እንደመታች ገልጻለች፡፡ ከሁለቱም ወገኖች በኩል ለተሰነዘረው ጥቃት መልስ እንደኾነ የእስራኤል ሠራዊት አመልክቷል።

በጋዛ፣ በሦስት ሳምንታት ውስጥ የተገደሉት ሕፃናት ቁጥር፣ እ.አ.አ ከ2019 ወዲህ፣ በዓለም ላይ በነበሩ ግጭቶች ከተገደሉት ሕፃናት ቁጥር እንደበለጠ የሕፃናት አድን ድርጅት ገልጿል።

በእስራኤል-ሐማስ ጦርነት በሦስት ሳምንታት ውስጥ፣ ከሦስት ሺሕ በላይ ሕፃናት እንደተገደሉ፣ ድርጅቱ አስታውቋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ በበኩላቸው፣ ኹኔታዎች “በየሰዓቱ ተስፋ አስቆራጭ እየኾኑ መጥተዋል፤” ካሉ በኋላ፣ “ፍልስጥኤማውያንን በጅምላ መቅጣት” እንዳይኖር አስጠንቅቀዋል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ትላንት እሑድ፣ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ነታንያሁ ጋራ በስልክ ተነጋግረዋል። ፕሬዚዳንቱ፣ እስራኤል ከሽብር ራሷን የመከላከል መብት እንዳላት በድጋሚ ገልጸው፣ ሲቪሎች ግን ከጥቃት እንዲጠበቁ በአጽንዖት አሳስበዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG