በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል ወታደሮች ባደረሱት ጥቃት አንድ ፍልስጤማዊ ተገደለ


ፍልስጤማዊው ተቃዋሚ በምዕራብ ባንክ ራማላህ ከተማ ከእስራኤል ጦር ወታደሮች በመጋጨቱ ወንጭፍ ሲጠቀም
ፍልስጤማዊው ተቃዋሚ በምዕራብ ባንክ ራማላህ ከተማ ከእስራኤል ጦር ወታደሮች በመጋጨቱ ወንጭፍ ሲጠቀም

በእስራኤል ወታደሮችና በፍልስጤማውያን መካከል ትናንት ማምሻውን በተፈጠረ ግጭት አንድ ፍልስጤማዊ ሲገደል፣ ሦስቱ ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲሉ የፍልስጤም የጤና ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

የዐይን ምስክሮች እንዳሉት ግጭቱ የተፈጠረው የእስራኤል ወታደሮች ጀኒን በተባለው የተፈናቃዮች ካምፕ ውስጥ ሰዎችን ለመያዝ በመጡበት ወቅት ነው።

የእስራኤል ወታደሮች በተኮሱት ጥይት የአንድ ፍልስጤማዊ ወጣት ህይወቱ አልፏል ሲሉ የፍልስጤም የጤና ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ሌሎች ሦስት ወጣቶችም በተተኮሰባቸው ጥይት ቆስለዋል፡፡ የእስራኤል ሰራዊት እንደሚለው ወታደሮቹ በአክራሪ ተዋጊነት የሚጠረጥሩትን ግለሰብ ለመያዝ በሞከሩበት ወቅት ነው ግጭቱ የተነሳው።

“ወደ ወታደሮቹ ፈንጂዎች ተወረወሩ፣ በተጨማሪም ተኩስ ተከፈተባቸው፤ ወታደሮቹም የተኩስ መልስ ሰጡ” ሲል ሰራዊቱ በመግለጫው አስታውቋል።

የሰሞኑ ሁከት የተሰማው ባለፈው መጋቢት ጽንፈኛ ተዋጊዎች የሰው ህይወት የቀጥፉ ጥቃቶችን ከፈፀሙ በኋላ፣ የእስራኤል ኃይሎች በዌስት ባንክ ጥቃት መጀመራቸውን ተከትሎ ነው።

XS
SM
MD
LG