በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶሪያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች በ"እስልምና መንግሥት" ተይዘው የነበሩ ይዞታዎችን አስለቀቁ

በዩናይትድ ስቴትስ የሚደገፉት የሶሪያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ዛሬ ማክሰኞ ባወጡት መግለጫ ከሶሪያዋ ራካ ከተማ “የእስልምና መንግሥት” ብሎ ራሱን በሚጠራው ቡድን ቁጥጥር ሥር የነበሩትን የመጨረሻዎቹን ይዞታዎች አስለቅቀው መቆጣጠራቸውን አስታወቁ።

በዩናይትድ ስቴትስ የሚደገፉት የሶሪያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ዛሬ ማክሰኞ ባወጡት መግለጫ ከሶሪያዋ ራካ ከተማ “የእስልምና መንግሥት” ብሎ ራሱን በሚጠራው ቡድን ቁጥጥር ሥር የነበሩትን የመጨረሻዎቹን ይዞታዎች አስለቅቀው መቆጣጠራቸውን አስታወቁ።

በኩሮዶችና በአረብ ሚሊሺያዎች የተዋቀረው የሶሪያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ቃል አቀባይ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል የራካው ውጊያ ተጠናቋል ብለዋል።

ብሪታንያ የሚገኘው የሶሪያ ሰብዓዊ መብቶች ቅኝት አካልም ራካ ነፃ ወጥታለች ሲል አስታውቋል።

የዲምክራሲያዊ ኃይሎቹ ተዋጊዎች የእስልምና መንግሥት የዕዝ ማዕከል ሆኖ ሲያገለግል የነበረውን አንድ ሆስፒታል ከተቆጣጠሩ በኋላ በከተማዋ የቡድኑ ዋና ሰፈር የነበረውን የኳስ ሜዳ ይዘውታል።

የእስልምና መንግሥት ተዋጊዎችን ከራካ የማስወጣት ጥቃቱ በዩናይትድ ስቴትስ በሚመራው ሕብረት የአየር ጥቃትና ሌላም ድጋፍ እየታገዘ የተጀመረው ባለፈው ሰኔ ወር እንደነበር ይታወሳል።

ራካ ዘጠና ከመቶ በሶሪያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች እጅ መግባቷን የዩናይትድ ስቴትስ መራሹ ሕብረት ቃል ኣአቀባይ ራያን ዲለን ተናግረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG