በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣ ሰሜናዊ ምስራቅ ግዛት፣ ባለፈው እሁድ ለተገደሉት 15 ሰዎች እስላማዊ መንግሥት ኃላፊነቱን የሚወስድ መሆኑን ትናንት ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
የተባበሩት የዴሞክራሲ ኃይሎች ወይም ኢዲፍ ተብሎ ራሱን የሚጠራው ድርጅት እኤአ ከ2019 ራሱን ከእስላማዊ ድርጅት ማቆራኘቱ ሲነገር እኤአ ከ1990 ጀምሮ በሰለማዊ ዜጎች ላይ በርካታ ጥቃቶችን ማድረሱ ተመልክቷል፡፡
እስላማዊ ቡድኑ አባሎቹ ባደረሱት ጥቃት ወደ 20 የሚጠጉ ክርስቲያኖችን መግደላቸውንና ስድስት ተሽከካሪዎችንም ማቃጠላቸውን አስታውቋል፡፡