በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍጋኒስታን በአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት አርባ ሰዎች ተገደሉ

አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ ከኢራን ጋር ግንኙነት ያለው የሺያ ሙስሊሞች የባህል ማዕከል የሚገኝበት ህንፃ ላይ በደረሰ አጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ከአርባ የሚበልጡ ሰዎች ተገደሉ። ሌሎች ሰማኒያ አራት ሰዎች መቁሰላቸውን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ገልፀዋል።

አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ ከኢራን ጋር ግንኙነት ያለው የሺያ ሙስሊሞች የባህል ማዕከል የሚገኝበት ህንፃ ላይ በደረሰ አጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ከአርባ የሚበልጡ ሰዎች ተገደሉ። ሌሎች ሰማኒያ አራት ሰዎች መቁሰላቸውን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ገልፀዋል።

በፍንዳታው ከተገደሉት መካከል አራት ሴቶችና ሁለት ህፃናት እንደሚገኙበት የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።

እስላማዊ መንግሥት ቡድን ለጥቃቱ ኃላፊነት ወስዷል። ከአሁን ቀደምም ካቡልና ሊሎችም ከተሞች ውስጥ በሺያዎች የፀሎት ቤቶችና ስብሰባዎች ላይ ለደረሱ ጥቃቶች ይሄው ቡድን ኃላፊነት ሲወስድ ቆይቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG