በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስላማዊ መንግሥት (አይኤስ) ብሎ ራሱን የሚጠራው ቡድን 11 የግብጽ ወታደሮች ለተገደሉበት ጥቃት ኃላፊነት ወሰደ


ከግብጽ ስዊዝ ቦይ በስተምስራቅ በሚገኝ የውሃ መሳቢያ ጣቢያ ላይ ለደረሰው እና ቢያንስ አስራ አንድ ወታደሮች ለተገደሉበት ጥቃት ግብጽ ውስጥ የሚንቀሳቀስ የእስላማዊ መንግሥት ቅርንጫፍ ቡድን ኃላፊነት ወሰደ።

ከትናንት በስተያ በተፈጸመው ጥቃት ከተገደሉት ሌላ ቢያንስ አምስት ፖሊሶች መቁሰላቸውን የሀገሪቱ የጦር ኃይል አስታውቋል። ጥቃቱ በቅርብ ዓመታት በግብጽ የጸጥታ ኃይሎች ላይ ከተደረሱት ከባድ ጥቃቶች አንዱ መሆኑ ተመልክቷል። ጽንፈኛው ቡድን ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደው አአማክ በሚባለው የዜና ማሰራጫው ላይ ባወጣው መግለጫ ነው።

ግብጽ በሲናይ ከእስላማዊ መንግሥት መር አማጽያን ጋር እየተዋጋች ስትሆን አመጹ እአአ በ2013 በህዝብ የተመረጡት እስላማዊው ፕሬዚዳንት በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣናቸው ከተገለበጡ ወዲህ ተባብሷል።

XS
SM
MD
LG