ዋሺንግተን ዲሲ —
እስላማዊ ልማት ባንክ ሶማሊያ ውስጥ የጀመረውን የብዙ ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት በሙስና በብልሹ አስተዳደር ውንጀላዎች ሳቢያ ማገዱ ተጠቆመ።
እኤአ በ2016 ጥቅምት ወር ላይ የቆላማ አካባቢዎች ልማት ፕሮጀክት በሦስት የገጠር መንደሮች የተጀመረው ለአርብቶ አደሮች ድርቅ ለመቋቋም የሚያስችሉ ዘዴዎች ለመገንባት የጤና እና የትምህርት አገልግሎቶችን ለማዳረስ እና የቀንድ ከብቶች እና አዝርዕት ጥራት ማሻሻያ ዘዴዎች ተደራሽነት ለማሳደግ ታልሞ እንደሆነ ተገልጿል።
ፕሮጄክቱ ባጠቃላይ ወጪው አምስት ሚሊዮን ዶላር እንደሚሆን ታቅዶ ከዚያ ውስጥ ባንኩ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮኑን ወደሶማሊያ ማዕከላዊ ባንክ ያለ የባንክ ሂሳብ በሦስት ጊዜ ክፍያ ማስገባቱ ነው የተገለፀው።
ይሁን እንጂ ባንኩ ባካሄደው የሂሳብ ቁጥጥር የልማት ፕሮጀክት እስካሁን ምን እንዳከናወነ በተጨባጭ የቀረበ ሪፖርት እንደሌለ ነው ኦዲተሮቹ የገለፁት።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ