በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እሥልምና ወደኢትዮጵያ የገባው እምነቱ ራሱ በተጸነሰበት ገደማ እንደሆነ ተገለጸ


የእሥልምና እምነት ኢትዮጵያ የገባው ከሞላ ጎደል እምነቱ ራሱ በአረብያ ምድር ከተጸንሰበት ጊዜ አንስቶ እንደሆነና በአብዛኛው በሰላማዊ መንገድ እንደተስፋፋ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም የታሪክ ተመራማሪ ዶክተር ክንዴ ነህ እንደግ ገልጸዋል።

የእሥልምና ታሪክና አስተምሮት እንደሚገልጸው ነብዩ ሞሐመድ በ 610 አመተ አለም (እአአ ማለት ነው) 40 አመት እድሜ ከሞላቸው ጊዜ ጀምሮ የአረብያ ህዝቦችን የቅዱስ ቁርአንን ትምህርት ማስተማር ጀመሩ። የነብዩ መሐመድ ስብከት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥቅማችንን ያሳጣናል በሚል ስጋት የመካ የነገድና የጎሳ አለቆችና ሹማምንት ነብዩ መሐመድንና ተከታዮቻቸውን ማዋከብ ጀመሩ። የማዋከቡና የማሳደዱ ተግባር እየከፈ ሲሄድ ነብዩ መሀመድ የተወሰኑ ተከታዮቻቸው ወደ ኢትዮጵያ እንዲሸሹ አደረጉ። በዛን ወቅት አክሱም የነበሩት የኢትዮጵያ ንጉስ ክርስትናን የተቀበሉ ሆነው ሳለ ሙስሊም ስደተኞቹን ተቀብለው በልዩ እንክብካቤና ፍቅር እንዳስተናገድዋቸው ዶክተር ካንዴ ገልጸውልናል።

ነብዩ መሐመድ የኢትዮጵያው ንጉስ ውለታን በማሰብ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን አትንኩ የሚል ትእዛዝ እንዳስተላለፉና በተከታታይ በመካከለኛው ምስራቅ በተነሱ የእስልማና ሃይሎች ሃያላን ዘንድ እንደጥብቅና የማይሻር መመርያ እንደተወሰደ ዶክተር ክንዴ ጠቅሰዋል።

የእሥልምና እምነት በፍጥነት በተስፋፋባቸው አከባቢዎች የሀይል እርምጃ የማይናቅ ሚና እንደነበረው በኢትዮጵያ ግን እስልምና በአብዛኛው በሰላማዊ መንገድ እንደተስፋፋ ይሁንና የኢትዮጵያ ስርወ-መንግስታት የኦርቶዶክስ ሃይሞኖት አራማጆች ስለነበሩ የክርስተና ሀይማኖትና የእስላም እምነት ግንኙነት በተወሰነ መልኩም ቢሆን የአድልዎ፣ የመገለልና የጭቆና ገጽታ እንደንበረው ዶክተር ክንዴ ነህ እንደግ አስገንዝበዋል።

XS
SM
MD
LG