እስላማዊ መንግሥት በኢራቅ እና በሶሪያ በማድረስ ላይ ያለው ጥቃት ካለፈው ዓመት ጋራ ሲነፃጸር እጥፍ ለመድረስ መቃረቡን የአሜሪካው ማዕከላዊ ዕዝ አስታውቋል።
ራሱን እንደገና ለማቋቋም በመሞከር ላይ ያለው አይሲስ፣ በያዝነው የፈረንጆች 2024 ዓ/ም የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ 153 ጥቃቶችን በሁለቱ ሃገራት ማድረሱን የአሜሪካው ማዕከላዊ ዕዝ ዛሬ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።
ቡድኑ ባለፈው 2023 ዓ/ም በሶሪያ እና ኢራቅ 121 ጥቃቶች እንዲፈጸሙ ማድረጉን አንድ ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ የአሜሪካ መከላከያ ባለ ሥልጣን አስታውቀዋል።
የማዕከላዊ ዕዙ መግለጫ የመጣው ቡድኑ ግዛቴ የሚላቸውን ሃገራት አውጆ፣ ጽንፍ የያዘ የእስልምና አተረጓጎምን አስፈናለሁ ብሉ ከተነሳ አሥር ዓመታት በተቆጠሩበት ወቅት ነው።
የጥቃቶቹ እየጨመሩ መምጣት ለበርካታ ዓመታት አቅሙ ተዳክሞ የነበረው አይሲስ እንደገና እራሱን ለማቋቋም በመሞከር ላይ መሆኑን የሚያመላክት እንደሆነ ማዕከላዊ ዕዙ ጠቁሟል።
መድረክ / ፎረም