በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል ምርጫ


እስራኤል በስድስት ወራት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ጠቅላላ ምርጫ እያካሄደች ነው። የቀድሞ ወታደራዊ ኃላፊ ቤኒ ጋንዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያንሚን ኔታንያሁን እየተገዳደሩ ነው ተብሏል።

ሁለተኛ ምርጫ እንዲካሄድ የተጠራው ባለፈው ሚያዚያ ወር ከተደረገው ምርጭ በኋላ ኔታንያሁ ከምክር ቤቱ 120 መቀመጫዎች ቢያንስ 61 መቀመጫ ያለው የብዙሃን የጥምረት መንግሥት ለመመስረት ባለመቻላቸው ነው።

እስራኤል ውስጥ በዘልማድ ከ65 እስከ 70 ከመቶ ህዝብ ለምርጫ ይወጣል። በዛሬው ሁለተኛ ዙር ምርጫ ግን ብዙ ሰው ላይመርጥ ይችላል የሚል ሥጋት የነበረ ቢሆንም በቂ የሰው ብዛት እየታየ መሆኑ ተገልጿል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG