በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢሣያስ ኢትዮጵያ ናቸው


የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ
የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ ለሁለት ቀናት ጉብኝት ኢትዮጵያ ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ ተገኝተው ከተቀበሏቸው በኋላ ሁለቱ መሪዎች በሃገሮቻቸው ትብብርና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይም መመካከራቸውን የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ዛሬ ትዊት አድርገዋል።

ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ ለኤርትራው ፕሬዚዳንት በቤተመንግሥቱ የምሳ ግብዣ ያደረጉ ሲሆን በግብዣው ላይ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የኤሮምያ ክልል ፕሬዚዳንት ሺመልስ አብዲሣም መገኘታቸውን ያመለከቱት የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ቀደም ሲል ባሰፈሩት ትዊት ላይ የጉብኝቱ ዓላማ በሃገሮቹ ትስስሮች፤ ኮቪድ-19ን በጋራ መዋጋት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መመካከርንም እንደሚያካትት ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ባሠፈሩት አጭር መልዕክት “ፕሬዚዳንቱ ለሁለት ቀናት በሚያደርጉት ቆይታ በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እናድርጋለን፤ ስለተጋፈጥናቸው ፈታኝ ሁኔታዎች እንወያያለን” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG