ዋሺንግተን ዲሲ —
ሃሪኬን ኢሳያስ የሚባለው ከባድ ዝናብ የያዘ የውቅያኖስ ማዕበል ምሥራቅ ዩናይትድ ስቴትስ ሰሜን ካሮላይናና ጠረፍ ደብድቦ በስተሰሜን እየገስገሰ ነው። ብሄራዊ የውቅያኖስ ማዕበል ማዕከል እንዳለው ኢሳያስ ከውቅያኖስ በፍጥነት ከተነሳ በኋላ የብሱ ላይ ደረሶ ፍጥነቱ ጋብ ብሏል።
ይሁን እንጂ በበርካታ አካባቢዎች ብዙ ሺህ መኖሪያ ቤቶችና የንግድ ድርጅቶችን የኤሌክትሪክ ኃይል አቋርጧል። ሰሜንና ደቡብ ካሮላይና ሌሎችም ክፍለ ግዛቶች ላይ መጠነ ሰፊ ዝናብ እንደሚያወርድ ተሰግቷል። ዋሽንግተን ዲሲና ቦልቲሞርም እንዲሁ የከባድ ዝናብና ጎርፍ አደጋ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።