ዋሽንግተን ዲሲ —
በኢራቅ የእስላማዊ መንግሥት(አይኤስ) አክራሪ ቡድኖች ከባግዳድ በስተሰሜን 120 ኪሎሜትር ላይ ወደሚገኝ አንድ የወታደሮች ጦር ሰፈር ውስጥ በመግባት በከፈቱት ተኩስ 11 ወታደሮችን በተኙበት መግደላቸው ተገለጸ፡፡
ስማቸውን ያልገለጹ ሁለት የኢራቅ የደኅንነት ባለሥልጣኖች ለአሶሼይትድ ፕሬስ እንዳስታወቁት ጥቃቱ የተፈጸመው በዲያላ ክልፍለ ግዛት አል አዚም አውራጃ ውስጥ ሲሆን፣ በአገሬው አቆጣጣር ዐርብ ከሌሊቱ 9 ዘጠኝ ሰዓት ላይ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
እስላማዊ ሚሊሺያዎቹ ባለፈው ጥቅምት የሺኣ አማኞች በሚበዙበት በዚሁ የዲያላ ክፍለ ግዛት ውስጥ፣ ተመሳሳይ ጥቃት በመፈጸም፣ ታግተው የተወሰዱ 11 ሰላማዊ ሰዎችን በመግደል ሌሎች በርካታ ሰዎችን ማቁሰላቸውን አሶሼይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
የአይኤስ ታጣቂዎች ከቅርብ ወራት ወዲህ የሚያደርጉት ጥቃት እያየለ መምጣቱ ተገልጿል፡፡
ባለፈው ሀሙስ ምሽት በሰሜን ምስራቅ ሶሪያ ውስጥ የታሰሩባቸው ሰዎችን ለማስቀቅ እስር ቤቱ ላይ ጥቃት መሰዘንራቸው ተመልክቷል፡፡
የአይኤስ እኤአ በ2014 በአብዛኛው የኢራቅና የሶሪያ ግዛት የእስላማዊ መንግሥት መመስረቱን በማወጅ የተቋቋመ ድርጅት መሆኑ ይታወሳል፡፡