ዋሺንግተን ዲሲ —
አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ አጥፍቶ ጠፊ ፍንዳታ ደርሶ ቢያንስ ሠላሳ አንድ ሰዎች ገደለ ከሥልሳ አምስት በላይ አቁስሏል።
አጥቂው ፍንዳታውን ያደረሰው በሺያ ሙስሊሞች መስጊድ አካባቢ ምዕመናን ተሰብስበው የፋርስ የዘመን መለወጫ ኖውሩዝን በዓል በማክበር ላይ ሳሉ መሆኑን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት እና ዕማኞች ገልፀዋል።
የእስልምና መንግሥት ቡድን ኃላፊነት ወስዷል። አጥፍቶ ጠፊው ፓኪስታናዊ መሆኑንም ሽብርተኛው ቡድን ተናግሯል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ