በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከ“እሥላማዊ መንግሥት” ከፍተኛ መሪዎች አንዱ ተገደለ


ሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ውስጥ በተካሄደ የድሮን ጥቃት የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ አድኖ ያገኘው ማሄር አል-አጋል የገደለበት ቦታ ላይ ፍርስራሹን ያሳያል፣ እአአ 12/2022
ሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ውስጥ በተካሄደ የድሮን ጥቃት የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ አድኖ ያገኘው ማሄር አል-አጋል የገደለበት ቦታ ላይ ፍርስራሹን ያሳያል፣ እአአ 12/2022

ከእሥላማዊ መንግሥት ቡድን ከፍተኛ መሪዎች አንዱን መግደሏን አሜሪካ ዛሬ አስታወቀች።

የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ አድኖ ያገኘውና እንደገደለው ያሳወቀው ማሄር አል-አጋል “አምስቱ ከፍተኞች” ተብለው ከሚጠሩት የሽብርተኛው የሽብር ቡድኑ አዛዦች አንዱ መሆኑ ተገልጿል።

አል-አጋል የተገደለው ሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ውስጥ በተካሄደ የድሮን ጥቃት መሆኑን፣ እራሱን የሚጠራው የሶሪያ ክፍለሃገር ገዥ እያለ እንደነበረ፣ የእሥላማዊ መንግሥት አስኳል አመራርንና በዓለም ዙሪያ ያሉ የቡድኑ አጋሮችን የሚያገናኝ ቁልፍ ሰው እንደነበረ እዙ አስታውቋል።

“እርምጃው ጠንካራ መልዕክት ያስተላልፋል” ብለዋል የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ትናንት በሰጡት መግለጫ።

“ሶሪያ ውስጥ የአል-አጋል መገደል ቁልፍ የሆነውን አሸባሪ ከጨዋታው ውጭ በማውጣት የአይሲስን ዕቅድ፣ አቅምና በአካባቢው የሚያካሂደውን ዘመቻ በከፍተኛ ደረጃ ዝቅ ያደርገዋል” ብለዋል ባይደን በመግለጫቸው።

XS
SM
MD
LG