በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአይአርሲ ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝት


ፎቶ ፋይል፦ አይአርሲ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ሚሊባንድ
ፎቶ ፋይል፦ አይአርሲ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ሚሊባንድ

በዓለም ዙሪያ በሰብዓዊ ቀውሶች የተጎዱ ሰዎችን የሚረዳው ግብረ ሰናይ ድርጅት አይአርሲ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ሚሊባንድ ትናንት ማክሰኞ በኢትዮጵያ ቀርሳ አካባቢ ጉብኝት አድርገዋል።

በዚያ ግብረ ሠናይ ድርጅቱ በሚያካሂደው የሴቶች እና የህጻናት ጥበቃ መርኃ ግብር ከሚረዱ ነዋሪዎች ጋር ተነጋግረዋል።

ማዕከሉ በድርቅ ለተጎዱ ነዋሪዎች የገንዘብ ድጋፍ ለማድረስ እንዲሁም የንጹህ ውሃ እና የንጽህና አገልግሎቶች በማቅረብ እየሰራ መሆኑ ተመልክቷል።

ፕሬዚዳንቱ ዴቪድ ሚሊባንድ ባደረጉት ንግግር፣ "የአየር ንብረት ቀውስ ዓለም አቀፋዊ ችግር ነው። ይሁን እንጂ ከአየር ንብረት ተያያዥ የሆኑ አደጋዎች እየጨመሩ እና እያተባባሱ ባሉበት በአሁኑ ወቅትም ጭምር ቀውሶቹን የመቋቋሙ አቅም ጉዳይ ለየማኅበረሰቡ ተትቷል። ይህም የሚከሰቱ አደጋዎች፣ የረሃብ ቸነፈር እና መፈናቀል እንዲቀጥል ያደርጋል" ብለዋል።

XS
SM
MD
LG