በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢራቅ ሦስት ተቃዋሚዎች በፀጥታ ኃይሎች ተገደሉ


የኢራቅ ባለሥልጣኖች ዛሬ በገለጹት መሰረት ካርባላ በተባለችው የኢራቅ የተቀደሰች ከተማ ላይ ሦስት ተቃዋሚዎች በፀጥታ ኃይሎች በተከፈተባቸው ተኩስ ተገድለዋል። ግድያው የተፈፀመው ትላንት ሌሊት ሲሆን አንድ ቡድን የኢራን ቆንስላ ባለበት ግንብ ላይ ለመውጣት ከሞከረ በኋላ እንደሆነ ተገልጿል።

ትናንት ሌሊት በቦታው ላይ የተሰባሰቡ ተቃዋሚዎች “ኢራን ትውጣ፣ ካርባላ ነጻ ትሁን” የሚል መፈክር ያሰሙ እንደነበር ተዘግቧል።

ተኩሱ ከመከፈትዩ በፊት ተቃዋሚዎች የኢራን ቆንስላ ባለበት ግንብ ላይ የተለያዩ ነገሮችን ይወረውሩ እንዳነበርና እሳት ለማቀጣልም እንደሞከሩ ባለሥልጣኖች ተናግረዋል።

ኢራቅ ውስጥ ባለፈው ወር ተቃውሞ ከተነሳበት ጊዜ አንስቶ ከ 250 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG