ዋሺንግተን ዲሲ —
ዩናይትድ ስቴትስ ኢራቅና ሶርያ ባሉ በኢራን የሚደገፉ ሚሊሻዎች ላይ የአየር ድብደባ ማካሄድዋን በማውገዝ ተቃውሚዎች የኤምባሲውን ጊቢ የመጀመሪያ ጠርዝ መጣሳቸው ተዘግቧል።
በብዙ ሺህ ከሚቆጠሩት ተቃዋሚዎች መካከል አንዳንዶቹ እሳት ለኩሰዋል፣ ዲንጋይ ወርውረዋል፣ የሚሊሻ ቡድኖቹን በመደገፍ ባንዲራዎች አውለብልበዋል።
የዪናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዮ ከኢራቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐደል ዐብዱል ማህዲና ክፕረዚዳንት ባርሃም ሳሊሕ ጋር ስለሁኔታው በስልክ ተነጋግረዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ