በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ከግድያ ተረፉ


ጥቃቱ የደረሰበት ሥፍራ
ጥቃቱ የደረሰበት ሥፍራ

የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ አል ካድኺሚ ከተቃጣባቸው የድሮን ግድያ ሙከራ መትረፋቸውን የኢራቅ መንግሥት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡

መግለጫው እንዳስታወቀው ፣ አረንጋዴው ዞን ተብሎ በተከለለው ስፍራ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በሁለት ድሮኖች ተጭነው የተላኩ ቦምቦች የተጣሉ ሲሆን፣ ጠባቂዎቻቸው የተጎዱ ቢሆንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን ተርፈዋል ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩም ባስተላለፉት የትዊት መልዕክት “እግዚአብሄር ይመሰገን፣ ይኸው ተርፌ በሰዎቼ መካከል እገኛለሁ” ብለዋል፡፡

የባግዳድ ነዋሪዎች የዲፕሎማቶችን መኖሪያ በሆነው አካባቢ ትልቅ የፍንዳታ ድምጽና የተኩስ ልውውጥ መስማታቸውን አሶሼይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

በኢራን የሚደገፉ ሚሊሻዎች ባለፈው ወር የተካሄደውን የምክር ቤት አባላት ምርጫ ውጤት አለመቀበላቸውን ከገለጸ በኋላ በኢራቅ ውጥረቱ እየጨመረ መምጣቱ ተነገሯል፡፡

XS
SM
MD
LG