ዋሺንግተን ዲሲ —
የኢራቅ ኃይል የኢራቅ ወታደራዊ ኃይል “እስላማዊ መንግሥት ነኝ” በሚለው ፅንፈኛ እስላማዊ ቡድን ቁጥጥር ሥር ያሉትን የመጨረሻ ቦታዎችን ለማስለቀቅ ጥቃት ከፍቷል።
የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይዳር አል አባዲ አል ኳምና ራካ ላይ የቀሩት የፅንፈኛው ቡድን ጂሐዳውያን ያላቸው አማራጭ “ሞት ወይም እጅ መስጠት ነው” ሲሉ ዛሬ የጥቃቱን መከፈት አስታውቀዋል።
የኢራቅ ሃይሎች ፅንፈኛው ቡድን ከሦስት ዓመታት ወዲህ ከተቆጣጠራቸው ግዛቶች ከ90 ከመቶ በላይ የሚሆኑትን የኢራቅ ወታደራዊ ኃይል ማስለቀቁ ታውቋል። የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ኃይል እንደሚለው 1,500 የሚሆኑ የዳዕሽ አማፅያን አል ኩዋም አካባቢ ቀርተዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ