በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢራቅ ኩርዶች የነፃነት ውሳኔ ሕዝብ እያካሄዱ ነው


የኢራቅ ኩርዶች፣ በሰፊው ተቀባይነት ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቅ የነፃነት ውሳኔ ሕዝብ እያካሄዱ ሲሆን፣ ባግዳድ ያለውን መንግሥት ጨምሮ ከጎረቤት ሀገሮችና ከዩናይትድ ስቴትስ ግን ተቃውሞ ገጥሞታል።

የኢራቅ ኩርዶች፣ በሰፊው ተቀባይነት ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቅ የነፃነት ውሳኔ ሕዝብ እያካሄዱ ሲሆን፣ ባግዳድ ያለውን መንግሥት ጨምሮ ከጎረቤት ሀገሮችና ከዩናይትድ ስቴትስ ግን ተቃውሞ ገጥሞታል።

በኢራቅ ሰሜናዊ ምሥራቅ የሚገኘውና ከፊል ነፃ የሆነው የኩርድ ግዛት ፕሬዚደንት ማሳውድ ባርዛኒ ድምፅ ለመስጠት ብቁ የሆነው 5ሚሊዮን መራጭ በዛሬው ቀን ለነፃነት ድምፁን እንዲሰጥ ጥሪ አድርገዋል።

ፕሬዚደንቱ ትናንት ኤርቤል ውስጥ ባሰሙት ቃል

“ነፃ መሆናችን ያለፈውን አሰቃቂ ስህተት ላለመድገም ይረዳናል” ብለው፣ “ከእንግዲህ ከኢራቅ ጋር ያለን ግንኙነት ላንመለስበት ተቋርጧል” ሲሉም የውሳኔ ሕዝቡን መካሄድ አጠናክረዋል።

የውሳኔ ሕዝቡ የመጨረሻ ውጤት ነገ ማክሰኞ ይገለፃል ተብሎ ይጠበቃል።

ውሳኔ ሕዝቡ የኩርዶችን አዎንታ ቢያገኝ ነፃነት ይታወጃል ማለት እንደዳልሆነ፣ ነገር ግን የመለየት ድርድር ለማካሄድ የመጀመሪያ እርምጃ ይሆናል ነው የተባለው።

ፕሬዚደንት ባርዛኒ ባለፈው ሳምንት ለቪኦኤ የፋርስ አገልግሎት በሰጡት ቃል፣ ከውሳኔ ሕዝቡ በኋላ የኩርድ መንግሥት ከኢራቅ ባለሥልጣናት ጋር መደራደር እንደሚጀምር አስታውቀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG